በጎፋ ዞን በደረሰ ድንገተኛ የመሬት ናዳ አደጋ የሟቾች ቀጥር ከ220 ማለፉ ተገለፀ
በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ትናንት ጠዋት ድንገተኛ የመሬት ናዳ አደጋ ደርሷል
የነፍስ አድን ሥራው ተጠናክሮ መቀጠሉን የሟቾች ቁጥር ከዚህ በላይ ሊያሻቅብ እንደሚችል ዞኑ አስታውቋል
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጎፋ ዞን በገዜ ጎፋ ወረዳ በኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ ትናንት ጠዋት በደረሰ የመሬት ናዳ አደጋ የበርካች ህይወት ማለፉ ተገለጸ።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በመሬት ናዳ ሳቢያ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 229 መድረሱ ተገለጸ።
የገዜ ጎፋ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ምስክር ምትኩ የሟቾች ቁጥር 229 መድረሱን መናገራቸውን የደቡብ ሬድዮና ቴቬቪቭን ድርጅት ዘገባ ያመለክታል።
እስካሁን በተደረገው ፍለጋ ሴቶችና ሕፃናትን ጨምሮ 148 ወንዶች እና 81 ሴቶች በድምሩ የ229 ሰዎች አስክሬን የተገኘ ሲሆን፣ የአስክሬን ፍለጋ አሁንም ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልጸዋል።
የሟቾች ቁጥር ከዚህ በላይ ሊያሻቅብ እንደሚችልና የነፍስ አድን ሥራው ተጠናክሮ መቀጠሉን ተናግረዋል።
አደጋው መጀመሪያ ሶስት ቤተሰብ ላይ መድረሱን ያስታወቁት በገዜ ጎፋ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ምስክር ምትኩ፤ ይህንን ሰምተው እነሱን ለማዳን ርብርብ በሚደረግት ወቅት ድጋሚ ባጠመ የናዳ አደጋ የበርካቶች ህይወት ማለፉን አስታውቀዋል።
በአደጋው ሰለባ ከሆኑት ሰዎች መካከል የወረዳው ፖሊስ አባላትን ጨምሮ ሴቶችና ሕፃናት እንደሚገኙበትም አስተዳዳሪው አስታውቀዋል።