ለተከታታይ 7 ቀናት በጣለው ዝናብ ምክንያት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ችግር ውስጥ ገብተዋል
በህንድ የተከሰተውን ከባድ ጎርፍ ተከትሎ በተፈጠረው የመሬት መንሸራተት እስካሁን በትንሹ የ125 ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን የነፍስ አድን ሰራተኞች ከሰመጡ ቤቶች ላይ ጭቃ በማንሳት ላይ እየተረባረቡ ይገኛሉ፡፡
ባለሙያዎች እንደሚሉት ከሆነ ማህራሽተራ ግዛት በራት አስርት አመታት ውስጥ በከፍተኛ የመሬት መንሸራተት አደጋ ተጠቅታለች፡፡ ለተከታታይ ሰባት ቀናት በጣለው ዝናብ ምክንያት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ችግር ውስጥ ጥሏል፤ በርካታ ወንዞችም ገንፍላው ከመፍሰሻቸው እንዳይወጡ ተሰግቷል፡፡
የንግድ ማእከል ከሆነችው ሙምባይ በ180 ኪመየ ርቀት ላይ በምትገኘው ታሊይ ከተማ የሟቾች ቁጥር 42 ደርሷል፤ የመሬት መንሸራተቱ ብዙ ቤቶች መሬት ውስጥ እንዲቀበሩ ማድረጉን የማህራሽተራ ባለስልጣን ተናግረዋል፡፡
ባለስልጣናቱ እንዳሉት እስካሁን 40 ሰዎቸ በጭቃው ተይዘዋል፤ እነዚህን ሰዎች ለ36 ሰአታት ስለቆ በህይወት የማግኘቱ ሁኔታ ጠባብ መሆኑን ሮይተርስ ባለስልጣናት ጠቅሶ ዘግቧል፡፡
በቅርቡ የተፈጠረው ከባድ የሆነ የአየር ንብረት ሁኔታ በተለያዩ የአለም ሀገራት ማለትም በቻይና፣ በምእራብ አውሮፓና በሰሜን አሜሪካ ጉዳተ ያስከተለ ሲሆን ሁኔታው የአየር ንብረት ለውጥን ስጋትን ከፍ አድርጎታል፡፡