የቀድሞ ፕሬዘዳንት ዙማን መታሰር ተከትሎ የተፈጠረው ሁከት ወደ ጆሃንስበርግ ተዛመተ
ፕሬዝዳንት ሲርል ራማፎሳ “ለብጥብጥ የሚያበቃ ምንም ዓይነት ምክንያት የለም” ብሏል
የዙማ ቅጣት በድህረ-አፓርታይድ ህግ እና ፍትሃዊነት የማስፈፀም አቅም እንደመፈተን ተደርጎ ተወስዷል
የቀድሞ የደቡብ አፍሪካ ፕሬዘዳንት ጃኮብ ዙማን መታሰር ተከትሎ የደቡብ አፍሪካ ሁከት ወደ ጆሃንስበርግ ተዛመተ፡፡
የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ጃኮብ ዙማ መታሰራቸውን ተከትሎ አልፎ አልፎ ሲከሰቱ የነበሩ ሁከቶች ወደ ተለያዩ ከቶሞች እየተዛመቱ መሆናቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡በትናንትናው ዕለት ሌሊቱን በርካታ ሱቆች እንደተዘረፉ፣ የአውራ ጎዳና አንድ ክፍል እንደተዘጋ እና ዱላ የያዙ ሰልፈኞች ወደ ጆሃንስበርግ ሲያቀኑ እንደነበርም ነው የተገለጸው ፡፡
ብጥብጡ በዋነኝነት ያተኮረው ዙማ በተወለደበት የካዙል ናታል ግዛት ነው ተብለዋል፡፡
ፕሬዝዳንት ሲርል ራማፎሳ “ለብጥብጥ የሚያበቃ ምንም ዓይነት ምክንያት እንደሌለና ድርጊቱ በ COVID-19 ወረርሽኝ ሳቢያ የተዳከመው ኢኮኖሚ መልሶ ለመገንባት የሚደረገውን ጥረት የሚጎዳ ነው” ብለዋል::
የዙማ ቅጣት እና እስራት ሀገሪቱን በድህረ-አፓርታይድ ከ27 ዓመታት በኋላ ህግ እና ፍትሃዊነት በሀያላን ፖለቲከኞች ላይ የማስፈፀም አቅም እንደመፈተን ተደርጎ ተወስዷል፡፡ምንም እንኳን ቅጣቱ የዙማ ደጋፊዎችን ያስቆጣ ከመሆኑም በላይ በኤ.ኤን.ሲ ውስጥ አለመግባባቶችን የፈጠረ ቢሆንም፡፡
ፖሊስ ወንጀለኞች ቁጣውን ተጠቅመው ለመስረቅና ጉዳት ለማድረስ እየተጠቀሙበት መሆኑን ተናግሯል፡፡
የሀገሪቱ የብሔራዊ መረጃ ባለስልጣን/NatJOINTS/ ብጥብጥን በሚቀሰቅሱ ሰዎች ላይ የወንጀል ክስ ሊመሰረትባቸው እንደሚችል አስጠንቅቋል፡፡
የመረጃ ባለስልጣኑ በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው ሁከት ከተነሳበት ጊዜ አንስቶ 62 ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡
የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዘዳንት ጃኮብ ዙማ እጄን ለፖሊስ እጅ አልሰጥም ሲሉ ከቆዩ በኋላ ሐሙስ ጠዋት እጅ መስጠታቸው ይታወሳል።
የ 79 ዓመቱ የቀድሞ የደቡብ አፍሪከ ፕሬዚዳንት ጃኮብ ዙማ እስር ቤት መግባቸው እንዲዘገይ ያቀረቡት ማመልከቻ በፒተርማርቲዝበርግ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውድቅ መደረጉን ተከትሎ ዙማ በማረምያ ቤት እንዲቆዩ መደረጉንም ጭምር፡፡
ዙማ ካላፈው ሐሙስ አንስቶ የ 15 ወራት እስራታቸው ጀምረዋል፡፡