ፕሬዘዳንት ዙማ መረጃ ለመስጠት ባለመተባበራቸው ለፍርድቤት ንቀት አሳይተዋል በሚል የ15 ወራት እስር ተላልፎባቸዋል
የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዘዳንት ጃኮብ ዙማ በህግ ቁጥጥር ስር የሚውሉበት ቀን እየተቃረበ ባለበት ወቅት በመኖሪያ ቤታቸው ዙሪያ ለተሳበሰቡ በመቶዎች ለሚቆጠሩ ደጋፊዎቻቸው መብታቸው መጣሱን ተናግረዋል፡፡
ፖሊስ ፕሬዝዳንቱ እጃቸውን ለፖሊስ እንዲሰጡ የ5 ቀናት ቀነ ገደብ ማስቀመጡን አስታውቋል፡፡
ፕሬዘዳንቱ በሀገሪቱ ፍርድቤት ህገመንግስታዊ መብታቸው መጣሱን ገልጸዋል፡፡ ፕሬዘዳንቱ ፍርድቤቱ ለሚያደርገው የሙስና ወንጀል ምርመራ መረጃ ለመስጠት ሲጠየቁ በተደጋጋሚ ባለመተባበራቸው፣ ለፍርድቤቱን ንቀት አሳይተዋል በሚል የ15 ወራት እስር ተላልፎባቸው ነበር፡፡
ፕሬዘዳንቱ የሚታሰሩ ከሆነ ደጋፊዎቻቸው በደቡብ አፍሪካ አመጽ እናስነሳለን ሲሉ ዝተዋል፡፡
ፍርድቤቱ በፕሬዘዳንቱ ላይ ፍርድ ካስተላለፈ በኋላ የፕሬዘዳንቱን አቤቱታ ሊቀበል እንደሚችል አስታውቋል፡፡ ፕሬዘዳንቱ እጅ የሚሰጡበት ጊዜ በመጭው እሁድ የሚያቃ ቢሆንም የ79 አመቱ ጃኮብ ዙማ እጅ ለመስጠት ያሳዩት ምልክት የለም፡፡
“እዚህ ፖሊሶችን ሳይ እንዴት እንደሚይዙኝ ይገርመኛል፣ እንዴት ይህን ሁሉ ሰው አልፈው ይይዙኛል“ በማለት ጃኮብ ዙማ በደቡብ አፍሪካ ባለስልጣናት ላይ ማሾፋቸውን ቀጥለዋል፡፡
“የፖሊስ ኃላፊው ቤኪ ሴሊ ፕሬዘዳንቱን ለመያዝ የሚመጣ ከሆነ መጀመሪያ እኛን መያዝ ዘለበት” ብለዋል ሌንዶኩል ማፓላላ የተባሉ ደጋፊ፡፡ ዙማን ለመያዝ የታዘዙ ፖሊስች አስፈላጊ ከሆነ የፕሬዘዳንቱን ደጋፊዎች ለመቆጣጠር በግዛቱ የተለያዩ አካባቢዎች ይሰፍራሉ ተብሏል፡፡
ፕሬዘዳንት ዙማ እጅ ለመስጠት ፍቃደኛ ካልሆነ ፖሊስ ተጨማሪ ሶስት ቀናት ጊዜ ይሰጣቸዋል ተብሏል፡፡ ቻትሊን ፖዌል የተባሉ የደቡብ አፍሪካ የህግ ፕሮፌሰር ለኤኤፍፒ እንደተናገሩት የዙማን አቤቱታ መስማት የህገመንግስታዊ ፍርድቤቱን ወሳኔ አያስቆመውም ብለዋል፡፡