የአሜሪካ አጋማሽ ዘመን የምክር ቤት ምርጫ ዲሞክራቶች ሴኔቱን መቆጣጠራቸው ተነገረ
ከሰሞኑ ሲጠበቅ በነበረው የምርጫ ውጤት ዲሞክራቶች አብላጫ ወንበር በመያዝ የበላይ ሆነዋል
አዲስ የተመረጠው ሴኔት በፈረንጆቹ ጥር 3 ቃለ መሃላ ይፈጸማል
የአሜሪካ አጋማሽ ዘመን የምክር ቤት ምርጫ ዴሞክራ እና ሪፐብሊካን ፓርቲዎች አንገት ለአንገት ተያይዘው ሰንብተዋል።
በአጋማሽ ዘመን ምርጫው ዲሞክራቶች የላይኛው ምክር ቤት የሴኔትን አብላጫ ወንበር መቆጣጠራቸው ተነግሯል።
ዴሞክራቶች አሁን 50 የሴኔት መቀመጫዎች ሲኖራቸው፣ ሪፐብሊካኖች ደግሞ በአሁኑ ጊዜ 49 ወንበሮች አሏቸው።
የተሰጡ ድምፆችን ሲቆጠር የሰነበተ ሲሆን ሪፐብሊካኖች የተወካዮች ምክር ቤትን ለመቆጣጠር ተቃርበው ነበር ተብሏል።
ዴሞክራቶች ቢያንስ 50 የሴኔት መቀመጫዎችን ይቆጣጠራሉ የተባለ ሲሆን፤ ምክትል ፕሬዝዳንት ካማላ ሃሪስ 100 አባላት ባለው ምክር ቤት የማሸነፊያ ቁልፍ መሆናቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በሚያስደንቅ ሁኔታ መደሰታቸውን እና ሪፐብሊካኖች “ማን እንደሆኑ” የሚወስኑበት ጊዜ አሁን ነው ብለዋል።
"አሜሪካ በዲሞክራሲያችን እናምናለን፣የዲሞክራሲ ጥልቅ እና ጠንካራ መሆኑን አሳይታለች"ሲሉ የሴኔቱ የአብላጫ ድምጽ መሪ ቹክ ሹመር ተናግረዋል።
ሴኔት በአሁኑ ጊዜ በዲሞክራቶች እና በሪፐብሊካኖች መካከል 50 ለ50 ተከፍሏል።
የሴኔት ቁጥጥር በዴሞክራቶች የበላይን ከወደቀ እንደ የፌደራል ዳኞችን የመሰሉ የፕሬዝዳንት የዠባይደን እጩዎችን ማጽደቅ ይችላሉ ማለት ነው።
አዲስ የተመረጠው ሴኔት በፈረንጆቹ ጥር 3 ቀን ቃለ መሃላ ይፈጸማል።