የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ሩሲያ እና ዩክሬንን ለማሸማገል ፍላጎት አሳዩ
እርሳቸው ፕሬዝዳንት ቢሆኑ ጦርነቱ እንደማይጀመር ትራምፕ ተናግረዋል
አሜሪካ ከሩሲያ ነዳጅ ማስተላለፊያ ጥቃት ጀርባ እንዳትኖርም ትራምፕ አስጠንቅቀዋል
የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሩሲያን-ዩክሬንን ለማሸማገል ፍላጎት አሳዩ።
ከፈረንጆቹ 2016 እስከ 2020 ድረስ አሜሪካንን በፕሬዝዳንትነት የመሩት ዶናልድ ትራምፕ ስለ ወቅታዊ የሩሲያ- ዩክሬን ጦርነት እና ከሞስኮ ወደ ስካንድቪዲያን ሀገራት በተዘረጋው ኖርድ ስትሪም ሁለት የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ጥቃት ጉዳይ አስተያየት ሰጥተዋል።
ትራምፕ እንዳሉት አሜሪካ ከዚህ ነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ጥቃት ጀርባ እጇ እንዳይኖር አስጠንቅቀዋል።
ይህ የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር በድርድር ሊፈታ የሚችል እንጂ በሌላ በምንም መንገድ አይፈታም ሲሉም ትራምፕ አክለዋል።
የሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት ሊከሰት የማይገባው ነው ያሉት የቀድሞው ፕሬዝዳንት እሳቸው በስልጣን ላይ ቆይተው ቢሆን ጦርነቱ እንደማይከሰት ተናግረዋል።
የሩሲያ ዩክሬን ልዩነት በድርድር የሚፈታ ነበር የሚሉት ዶናልድ ትራምፕ ሁለቱን ሀገራት ሊያስታርቁ እንደሚችሉም ፍንጭ ሰጥተዋል።
በተያያዘ ዜና አሜሪካ ለዩክሬን ተጨማሪ የ1 ነጥብ 1 ቢሊዮን ግምት ያለው የጦር ሙሳሪያ ድጋፍ ልታደርግ እንደሆነ አስታውቃለች።
በቀጣዮቹ ጥቂት ቀናት ውስጥ ወደ ዩክሬን ይላካል የተባለው ይህ አዲሱ የጦር መሳሪያ ድጋፍ አሜሪካ ከመጠባበቂያ መጋዝኗ ሳይሆን ከጦር መሳሪያ አምራች ኩባንያዎች የተውጣጣ ድጋፍ እንደሆነ ተገልጿል።