ጸረ-እስላም አክቲቪስቶች ቁርአን ማቃጠላቸውን ወይም ኮፒዎችን መቅደዳቸውን ተከትሎ ዴንማርክ እና ስዊድን በዚህ አመት ተከታታይ የሆኑ የተቃውሞ ሰልፎችን አስተናግደዋል
ዴንማርክ ቁርአንን በተመለከተ አዲስ ህግ አወጣች።
የዴንማርክ ፖርላማ በትናንትናው እለት በሀገሪቱ የቁርአንን ኮፒዎች ማቃጣል ህገወጥ የሚያደረግ ህግ ማውጣቱን ሮይተርስ ዘግቧል።
ይህ ህግ የወጣው፣ ሙስሊም ሀገራት በዴንማርክ በቅዱስ የእስላም መጽሀፍቶች ላይ የታየውን የመቅደድ እና የማነወር ተግባራት በጽኑ መቃወማቸውን ተከትሎ ነው።
ጸረ-እስላም አክቲቪስቶች ቁርአን ማቃጠላቸውን ወይም ኮፒዎችን መቅደዳቸውን ተከትሎ ዴንማርክ እና ስዊድን በዚህ አመት ተከታታይ የሆኑ የተቃውሞ ሰልፎችን አስተናግደዋል።
በሁለቱ ሀገራት የታዩት ጸረ-እስላም የሆኑ ተግባራት ከእስላም ሀገራት ጋር ፍጥጫ መፍጠራቸው፣ የኖርዲክ ሀገራት ድርጊቱን እንዲያግዱ አድርጓቸዋል።
ዴንማርክ ይህን ህግ በማውጣት ሀይማኖት መተቸትን ጨምሮ በህገመንግስት በተረጋገጠው የመናገር ነጻነት እና በብሄራዊ ደህንነት መካከል መመጣጠን ለመፍጠር ፈልጋለች ተብሏል።
በስዊድን እና በዴንማርክ ያሉ ተችዎች ማንኛውም አይነት ክልከላ በልፋት የተገኘውን የሊበራል ነጻነት በቀጣናው ያዳክማል ይላሉ።
"ታሪክ ፍርዱን ይሰጣል፣ የመጣው የመናገር ነጻነት እገዳ በእኛ የመጣ ነው ወይስ በውጭ ኃይል የሚለው ይታያል" ሲሉ ክልከላውን የተቃወሙት የጸረ-ስደተኛ መሪ ኢንገር ስቶጅበርግ ተናግረዋል።
የዴንማርክ ሴንተሪስ ጥምረት የሚመራው መንግስት ህጉ በመናገር ነጻነት የሚኖረው ተጽዕኖ በጣም ትንሽ ነው ብለዋል።
ህጉን የሚጥስ የገንዘብ ቅጣት ወይም እስከሁለት አመት የሚደረስ እስራት ይጠብቀዋል።
ከዴንማርክ በተጨማሪ ስዊድንም ተመሳሳይ ህግ ለማውጣት እያሰበች ነው ተብሏል።