የኢራኑ መሪ ካሚኒ ስዊድን ቁርዓን ያቃጠሉትን ግለሰቦች አሳልፋ እንድትሰጥ ጠየቁ
ካሚኒ ቁርዓንን ያራከሱ ሰዎች "እጅግ ጠንካራ የሆነ ቅጣት" እንዲቀጡና ሰዊድን ለእስላማዊ ሀገራት አስተላልፋ እንድትሰጥ ጠይቀዋል
ባለፈው ሰኔ ወር በስዊድን ዋና ከተማ ስቶኮሆልም መስጂድ ፊት ለፊት በተካሄደው ተቃውሞ ላይ ቅዱስ ቁርዓን መቃጠሉን ተከትሎ የተቀሰቀሰው ቁጣ አልበረደም
የኢራኑ መሪ ካሚኒ ቁርዓን ያቃጠሉ ግለሰቦች ተላለፈው እንዲሰጡ እና እንዲከሰሱ ጠይቀዋል።
ካሚኒ በዛሬው እለት እንደተናገሩት ቁርዓንን ያራከሱ ሰዎች "እጅግ ጠንካራ የሆነ ቅጣት" እንዲቀጡና ሰዊድን ለእስላማዊ ሀገራት አስተላልፋ እንድሰጥ ጠይቀዋል።
"ሁሉም የእስላም አባቶች ቁስዓንን የሚያራክሱ ጠንካራ ቅጣት እንዲቀጡ ተስማምተዋል። የሰዊድን መንግስት ኃላፊነት አጥፊዎችን በእስላማዊ ሀገራት ለሚገኝ የፍትህ ስርአት ማስረከብ ነው" ብለዋል ካሚኒ።
ባለፈው ሰኔ ወር በስዊድን ዋና ከተማ ስቶኮሆልም መስጂድ ፊት ለፊት በተካሄደው ጸረ-እስላም ተቃውሞ ላይ ቅዱስ ቁርዓን መቃጠሉን ተከትሎ የተቀሰቀሰው ቁጣ አልበረደም።
የስዊድን መንግስት ድርጊቱን አላስቆመም የሚል ጠንካራ ትችት ቀርቦበታል፤ ከአንዳንድ ሀገራት ጋርም ቅራኔ ውስጥ ገብቷል።
ከኢራን በተጨማሪ ኢራቅም በድርጊቱ የተቆጣች ሲሆን የስዊድን አምባሳደርን ጠርታ ማነጋገሯ ተገልጿል።
በቁርዓን በቃጠል የተበሳጩ ኢራቃውያን በስዊደን ኢምባሲ ላይ ጥቃት አድርሰዋል።
ጥቃቱን ተከትሎ ስዊድን በኢምባሲዋ ሰራተኞች ላይ ጉዳት ይደርሳል በሚል ስጋት ሰራተኞቹን በጊዜያዊነት ወደ ሌላ ቦታ አዛውራለች።