የሊቢያው ዴርና ግድብ ለምን ተደረመሰ?
አደጋውን ማዳን ይቻልስ ነበር?
አልፏልበዴርና ከተማ በደረሰው አደጋ የሟቾች ቁጥር ከ12 ሺህ
የሊቢያው ዴርና ግድብ ለምን ተደረመሰ?
በሊቢያ ዴርና ከተማ ባሳለፍነው ሳምንት በተከሰተ የግድብ መደርመስ አደጋ እስካሁን ከ12 ሺህ በላይ ሰዎች መሞታቸው ተረጋግጧል።
ለዚህ ገዳይ አደጋ መከሰት ዋናው ምክንያት ዳንኤል የተሰኘው ከባድ የአየር ወጀብ ሲሆን ዴርና የተሰኘው ግድብ ከአቅሙ በላይ ውሀ መያዙ እንደሆነ ተገልጿል።
ሰሜን አፍሪካ እንዲህ አይነት አደጋ ሲደርስበት የመጀመሪያው ሲሆን የአየር ንብረት ለውጥ ደግሞ ዋነኛው ምክንያት እንደሆነ ተገልጿል።
ባለሙያዎች እንዳሉት ይህን አደጋ ማስቀረት ይቻል ነበር የተባለ ሲሆን ሶስት ዋና ጉዳዮች ደግሞ ለአደጋው መከሰት በመነሻነት ተጠቅሷል።
የውሀ ደህንነት ባለሙያው ኢንጅነር ሀሰን አቡ አል ናጋ ለአልዐይን እንዳሉት ዴርና ግድብ የውሀ ደህንነት አደጋዎችን እንዲቋቋም ተደርጎ አለመሰራቱን ተናግረዋል።
በምስራቅ ሊቢያ የሚገኘው ይህ ግድብ ለመጠጥ ውሀ እና ለመስኖ ስራዎች እጅግ ጠቃሚ ግድብ እንደነበር ተገልጿል።
በወቅቱ በነበረው ከባድ ዝናብ ምክንያት የሜድትራኒያን ባህር ከፍተኛ ውሀ በአካባቢው በመኖሩ ዴርና ግድብም ከአቅሙ በላይ ውሀ መያዙ እና ጫና ለመቀነስ የተገነቡት የግድቡ ማስተንፈሻ በሚገባ አለመስራታቸው ለአደጋው በምክንያትነት ተጠቅሷል።
ግድቦች ገና ለመገንባት ሲታሰቡ አደጋዎች እና ድንገተኛ የውሀ መጥለቅለቆች እንደሚያጋጥሙ ታሳቢ ተደርገው መገንባት እንዳለባቸውም ባለሙያው ጠቅሰዋል።
የአየር ንብረት ለውጥ ባለሙያዎች እና ሌሎች ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ዳንኤል የተባለው ወጀብ አደጋ ሊያደርስ እንደሚችል አስቀድመው አስጠንቅቀው ነበር።
ይሁንና ሊቢያውያን በተለይም የዴርና ከተማ ነዋሪዎች ለቅድመ ማስጠንቀቂያ መረጃው ትኩረት እንዳልሰጡ እና አደጋውንም የከፋ እንዳደረገው ተገልጿል።