በሊባኖስ መዲና ቤሩት ማክሰኞ እለት በተከሰተው ከፍተኛ ፍንዳታ የሟቾች ቁጥር እየጨመረ ነው
በቤሩት ፍንዳታ የደረሰበትን ስፍራ መልሶ ለመገንባት 15 ቢ/ዶላር ያስፈልጋል
የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኤማኑኤል ማክሮን ዛሬ ጉዳት የደረሰበትን አካባቢ ጎብኝተዋል፡፡ በጉብኝቱ ወቅት አደባባይ የወጡ የቤሩት ነዋሪዎች የሀገሪቱ መሪዎች ስልጣናቸውን እንዲለቁ የጠየቁ ሲሆን ፕሬዝዳንት ማክሮንም የሀገሪቱ ባለስልጣናት ከኃላፊነት እንዲነሱ ድጋፍ እንዲያደርጉ ሰልፈኞቹ ጠይቀዋል፡፡ ሰልፈኞቹ ሊባኖስ ለገባችበት የኢኮኖሚ ቀውስ የሀገሪቱን መንግስት ተጠያቂ አድርገዋል፡፡
ፍንዳታው ለደረሰበት አካባቢ መልሶ ግንባታ እስከ 15 ቢሊዮን ዶላር ወጪ እንደሚጠይቅ የሀገሪቱ ባለስልጣናት አስታውቀዋል፡፡ ይህ ደግሞ በከፍተኛ የገንዘብ ችግር ዉስጥ ለምትገኘው ሊባኖስ እጅግ ፈታኝ ጥያቄ ነው፡፡ ፈረንሳይን ጨምሮ በርካታ የምዕራቡ አለም እና የገልፍ ሀገራት ለመልሶ ግንባታ ድጋፍ ሊያደርጉላት ቃል ገብተዋል፡፡