የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባለፉት ቀናት ያወጣውን የውጭ ምንዛሬ ተመን አስቀጥሏል
ኢትዮጵያ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርአት ተግባራዊ እንዲደረግ መወሰኗን ተከትሎ ባንኮች አዲሱን የምንዛሬ ተመን ተግባራዊ በማድረግ ላይ ይገኛሉ።
ባንኮች በማህራዊ ትስስር ገጻቸው ባጋሩት የነሃሴ 21 2016 የውጭ ምንዛሬ ተመን ዝርዝር ላይ የዋጋ ልዩነት ታይቶባቸዋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዛሬ ነሃሴ 21 2016 የውጭ ሀገር ገንዘቦችን የሚገዛበትን እና የሚሸጥበትን ዋጋ ይፋ ሲያደርግ የአንድ ዶላር መግዣ ዋጋን ሰሞኑን ሲገዛበት ከነበረው ጋር ተመሳሳይ ሲሆነ ዋጋ በ104.6038 ብር እየገዛ ይገኛል። መሸጫው ላይም በተመሳሳይ ጭማሪ ሳያደርግ 116.0579 ብር እየሸጠ ይገኛል።
የእንግሊዝ ፓውንድ በ130.5842 ብር እየገዛ በ145.5639 ብር እንደሚሸጥም አስታውቋል።
ዳሽን ባንክ ባለፈው ሳምንት ያወጣውን የውጭ ምንዛሬ ተመን በዛሬው እለትም አስቀጥሏል። ባንኩ አንድ ዶላር በ104.2016 ብር እየገዛ በ116.4798 ብር እየሸጠ እንደሚገኝ ይፋ አድርጓል።
ጸደይ ባንክ አንድ የአሜሪካ ዶላር በ106.58 ብር እየገዛ፤ በ117.24 እየሸጠ ነው።
በአዋሽ ባንክ አንድ የአሜሪካ ዶላር በ104.6249 ብር እየተገዛ በ117.1799 ብር እየተሸጠ መሆኑን ባንኩ ባወጣው እለታዊ የምንዛሬ ተመን ይፋ አድርጓል።
ሲዳማ ባንክ ደግሞ አንድ ዶላር በ105.8769 ብር ገዝቶ በ117.0919 ብር እየሸጠ ነው። ባንኩ የእንግሊዝ ፓውንድ በ120.8816 ብር እየገዛ በ128.1345 ብር እየሸጠ መሆኑንም ነው ባወጣው እለታዊ የውጭ ምንዛሬ ተመን ያመላከተው።
በኢትዮጵያ ልማት ባንክ አንድ የአሜሪካ ዶላር በ113.0200 ብር እየተገዛ በ117.0100 ብር እየተሸጠ መሆኑን ባወጣው እለታዊ የምንዛሬ ተመን ይፋ አስታውቋል።