የግል ንግድ ባንኮች ለአንድ ዶላር እስከ 124 ብር መግዣ እስከ 127 ብር መሸጫ ዋጋ አቅርበዋል
ኢትዮጵያ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርአት ተግባራዊ እንዲደረግ መወሰኗን ተከትሎ ባንኮች በየእለቱ የውጭ ምንዛሬ ተመን ይፋ ማድረጋቸውን ቀጥለዋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዛሬ ታህሳስ 8 ቀን 2017 ዓ.ም የውጭ ሀገር ገንዘቦችን የሚገዛበትን እና የሚሸጥበትን ተመን ይፋ ሲያደርግ ከ24 ቀናት በፊት ያወጣውን ዋጋ አስቀጥሏል። በዚህም አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ122.5986 ብር እየገዛ በ125.0506 ብር እየሸጠ መሆኑን አስታውቋል።
ዳሽን ባንክ እለታዊ የውጭ ምንዛሬ ተመኑን ይፋ ሲያደርግ ህዳር 16 2017 ያወጣውን ተመን ያስቀጠለ ሲሆን አንድ ዶላርን በ124.7171 ብር እየገዛ በ127.2114 ብር እየሸጠ መሆኑን ገልጿል።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ124.2116 ብር ገዝቶ በ126.6958 ብር እየሸጠ ነው።
ጎህ ቤቶች ባንክ አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ124.8705 ብር እየገዛ በ127.3679 ብር እየሸጠ መሆኑን የታህሳስ 8 2017 የውጭ ምንዛሬ ተመኑ ያሳያል።
ብርሃን ባንክ የምንዛሬ ተመኑ ላይ መጠነኛ የሳንቲም ጭማሪ አድርጓል። በዚህም አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ124.6483 ብር ገዝቶ በ127.1413 ብር እየሸጠ መሆኑን አስታውቋል።
ጸደይ ባንክ በውጭ ምንዛሬ ተመኑ ላይ መጠነኛ የሳንቲም ጭማሪ አድርጎ አንድ ዶላር በ124.7380 ብር ገዝቶ በ127.2328 ብር እየሸጠ እንደሚገኝ ገልጿል።