እስራኤል የአየርላንድ ኢምባሲዋን "በጸረ-እስራኤል ፖሊሲ" ምክንያት ልትዘጋ መሆኗን አስታወቀች
ባለፈው ግንቦት ወር አየርላንድ ለፍልስጤም የሀገርነት እውቅና መስጠቷን ተከትሎ እስራኤል አምባሳደሯን ጠርታለች
ደብሊን ደቡብ አፍሪካ በእስራኤል ላይ በአለምአቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት(አይሲሲ) ያቀረበችውን የዘር ማጥፋት ክስ በዚህ ሳምንት በመደገፏ እስራኤልን የበለጠ አናዷታል
እስራኤል የአየርላንድ ኢምባሲዋን "በጸረ-እስራኤል ፖሊሲ" ምክንያት ልትዘጋ መሆኗን አስታወቀች።
እስራኤል የአየርላንድ መንግስት ለፍልስጤም የሀገርነት እውቅና መስጠትን ጨምሮ እያራመደ ባለው "ጫፍ የረገጠ ጸረ-እስራኤል ፖሊሲ" ምክንያት የደብሊን ኢምባሲዋን ልትዘጋ እንደምትችል በትናንትናው እለት አስታውቃለች።
ባለፈው ግንቦት ወር አየርላንድ ለፍልስጤም የሀገርነት እውቅና መስጠቷን ተከትሎ እስራኤል አምባሳደሯን ጠርታለች።
ደብሊን ደቡብ አፍሪካ በእስራኤል ላይ በአለምአቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት(አይሲሲ) ያቀረበችውን የዘር ማጥፋት ክስ በዚህ ሳምንት በመደገፏ እስራኤልን የበለጠ አናዷታል።
የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ "በደብሊን ያለውን የእስራኤል ኢምባሲ ለመዝጋት ውሳኔ ላይ የተደረሰው የአየርላንድ መንግስት እያራመደ ባለው ጫፍ የረገጠ ጸረ-እስራኤል ፖሊሲዎች ምክንያት ነው።"
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጌዲዮን ሳአር የአየርላንድ መንግስት እያራመደ ያለው የጸረ-ጽዮናዊነት ተግባራት የአይሁዷን ሀገር ከመናቅ እና ከማንኳሰስ የመነጨ ነው ብለዋል።
የአየርላንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ስምኦን ሀሪስ ውሳኔው የሚያጸጽት መሆኑን እና ሀገራቸው ለሰብአዊ መብት መከበር እና ለአለምአቀፍ ህግ እንደምትቆም ተናግረዋል።
"አየርላንድ ጸረ-እስራኤል ነች የሚለውን ክስ አልቀበልም። አየርላንድ ሰላም ወዳድ፣ የሰብአዊ መብት እና አለምአቀፍ ህግ አክባሪ ነች" ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኤክስ ገጻቸው አስፍረዋል።
"አየርላንድ 'ቱ ስቴት ሶሉሽን' ተግባራዊ እንዲሆን እና እስራኤል እና ፍልስጤም በሰላም እንዲኖሩ ትፈልጋለች።"
የአየርላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሚካኤል ማርቲን የሁለቱ ሀገራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንደሚቀጥል እና በእስራኤል ያለውን የአየርላንድ ኢምባሲ የመዝጋት እቅድ እንደሌለ ተናግረዋል።