የኢትዮጵያ ልማት ባንክ 1 ዶላር መግዣን 113 ሲያደርስ፤ በ117 እየሸጠ ይገኛል
ኢትዮጵያ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርአት ተግባራዊ እንዲደረግ መወሰኗን ተከትሎ ባንኮች አዲሱን የምንዛሬ ተመን ተግባራዊ በማድረግ ላይ ይገኛሉ።
ባንኮች በማህራዊ ትስስር ገጻቸው ባጋሩት የነሃሴ 21 2016 የውጭ ምንዛሬ ተመን ዝርዝር ላይ የዋጋ ልዩነት ታይቶባቸዋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዛሬ ነሃሴ 21 2016 የውጭ ሀገር ገንዘቦችን የሚገዛበትን እና የሚሸጥበትን ዋጋ ይፋ ሲያደርግ የአንድ ዶላር መግዣ ዋጋን ሰሞኑን ሲገዛበት ከነበረው ጋር ተመሳሳይ ሲሆነ ዋጋ በ104.6038 ብር እየገዛ ይገኛል። መግዣው ላይም በተመሳሳይ ጭማሪ ሳያደርግ 116.0579 ብር እየገዛ ይገኛል።
የእንግሊዝ ፓውንድ በ130.5842 ብር እየገዛ በ145.5639 ብር እንደሚሸጥም አስታውቋል።
ንብ ባንክ አንድ የአሜሪካ ዶላር በ104.9086 ብር እየተገዛ በ117.4976 ብር እየተሸጠ መሆኑን ባወጣው እለታዊ የምንዛሬ ተመን ይፋ አድርጓል።
በኢትዮጵያ ልማት ባንክ ትናነት ጠዋት ላይ አንድ የአሜሪካ ዶላር በ110.0220 ብር እየተገዛ በ116.5000 ብር እየተሸጠ የነበረ ሲሆን፤ ከሰዓት በኋላ በለቀቀው የዋጋ ማሻሻያ አንድ የአሜሪካ ዶላር በ113.0220 እንደሚገዛ እና መሸጫውን ዋጋውን ደግሞ 117.0100 ማራሳን ኣሳተውቋል።
አዋሽ ባንክ አንድ የአሜሪካ ዶላር በ104.6249 ብር እየተገዛ በ117.1799 ብር እየተሸጠ መሆኑን ባወጣው እለታዊ የምንዛሬ ተመን ይፋ አስታውቋል።
ወጋገን ባንክ አንድ የአሜሪካ ዶላር በ104.7045 ብር እየተገዛ በ117.7926ብር እየተሸጠ መሆኑን ባወጣው እለታዊ የምንዛሬ ተመን አስታውቋል።