ዳሽን እና ንብ ባንክ የትናንቱን የውጭ ምንዛሬ ተመን አስቀጥለዋል
ኢትዮጵያ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ስርአት መከተል ከጀመረች 20 ቀናት ተቆጥረዋል።
ባንኮችም በማህራዊ ትስስር ገጻቸው የየእለቱን የውጭ ምንዛሬ ተመን ዝርዝር ይፋ ማድረጋቸውን ቀጥለዋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዛሬ ነሃሴ 11 2016 የውጭ ሀገር ገንዘቦችን የሚገዛበትን እና የሚሸጥበትን ዋጋ ይፋ ሲያደርግ የአንድ ዶላር መግዣ ዋጋን ትናንት ሲገዛበት ከነበረው ጋር በሳንቲሞች አሻሽሎ በ104.08 ብር እየገዛ ይገኛል። መግዣው ላይም በሳንቲሞች ጭማሪ አድርጎ በ115.32 ብር እየገዛ ይገኛል።
የእንግሊዝ ፓውንድ በ128.18 ብር እየገዛ በ142.68 ብር እንደሚሸጥ አስታውቋል።
ንብ ባንክ የእለቱን የውጭ ምንዛሬ ይፋ ሲያደርግ የትናንቱን አስቀጥሏል፤ አንድ የአሜሪካ ዶላር በ104.7514 ብር እየተገዛ በ117.3216 ብር እየተሸጠ መሆኑን ገልጿል።
ኦሮሚያ ባንክ አንድ የአሜሪካ ዶላር በ104.1571 ብር እየተገዛ በ117.6975 ብር እየተሸጠ መሆኑን ባወጣው እለታዊ የምንዛሬ ተመን ይፋ አድርጓል።
ዳሽን ባንክም በነሃሴ 10 2016 የውጭ ምንዛሬ ተመኑ ላይ ለውጥ ሳያደርግ አንድ የአሜሪካ ዶላር በ103.9999 ብር እየተገዛ በ116.4798 ብር እየተሸጠ ይገኛል።