የነሃሴ 27 የባንኮች የውጭ ምንዛሬ ዋጋ ምን ይመስላል?
ልማት ባንክና ሌሎች የግል ባንኮች 1 ዶላርን ከ105 እስከ 113 ብር እየገዙእስከ 118 እየሸጡ ይገኛል
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1 ዶላር በ105 ብር እየገዛ፤ በ117 እየሸጠ ይገኛል
ኢትዮጵያ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርአት ተግባራዊ እንዲደረግ መወሰኗን ተከትሎ ባንኮች አዲሱን የምንዛሬ ተመን ተግባራዊ በማድረግ ላይ ይገኛሉ።
ባንኮች በማህራዊ ትስስር ገጻቸው ባጋሩት የነሃሴ 27 2016 የውጭ ምንዛሬ ተመን ዝርዝር ላይ የዋጋ ልዩነት ታይቶባቸዋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዛሬ ነሃሴ 27 2016 የውጭ ሀገር ገንዘቦችን የሚገዛበትን እና የሚሸጥበትን ዋጋ ይፋ ሲያደርግ የአንድ ዶላር መግዣ ዋጋን ሰሞኑን ሲገዛበት በነበረበት ተመሳሳይ በሆነ ዋጋ በ105.4304 ብር እየገዛ ይገኛል። መሸጫው ላይም ጭማሪ ሳያደርግ 117.0277 ብር እየገዛ ይገኛል።
የእንግሊዝ ፓውንድ በ132.5631 ብር እየገዛ በ147.8322 ብር እንደሚሸጥም አስታውቋል።
ንብ ባንክ አንድ የአሜሪካ ዶላር በ104.9086 ብር እየተገዛ በ117.4976 ብር እየተሸጠ መሆኑን ባወጣው እለታዊ የምንዛሬ ተመን ይፋ አድርጓል።
በኢትዮጵያ ልማት ባንክ በለቀቀው እለታዊ የውጭ ምንዛሬ የዋ ዝርዝር አንድ የአሜሪካ ዶላር በ113.0200 እንደሚገዛ እና መሸጫውን ዋጋውን ደግሞ 117.0100 ማራሳን ኣሳተውቋል።
ወጋገን ባንክ አንድ የአሜሪካ ዶላር በ105.4338 ብር እየተገዛ በ118.6131 ብር እየተሸጠ መሆኑን ባወጣው እለታዊ የምንዛሬ ተመን ይፋ አስታውቋል።
አቢሲኒያ ባንክ አንድ የአሜሪካ ዶላር በ105.4407 ብር እየተገዛ በ118.0936ብር እየተሸጠ መሆኑን ባወጣው እለታዊ የምንዛሬ ተመን አስታውቋል።