የታህሳስ 15 2017 የባንኮች የውጭ ምንዛሬ ተመን ምን ይመስላል?
የግል ንግድ ባንኮች ለአንድ ዶላር እስከ 124 ብር መግዣ እስከ 127 ብር መሸጫ ዋጋ አቅርበዋል
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1 ዶላርን በ123 ብር እየገዛ በ126 ብር እየሸጠ ነው
ኢትዮጵያ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርአት ተግባራዊ እንዲደረግ መወሰኗን ተከትሎ ባንኮች በየእለቱ የውጭ ምንዛሬ ተመን ይፋ ማድረጋቸውን ቀጥለዋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዛሬ ታህሳስ 15 ቀን 2017 ዓ.ም የውጭ ሀገር ገንዘቦችን የሚገዛበትን እና የሚሸጥበትን ተመን ይፋ ሲያደርግ የሰሞኑን አስቀጥሏል። ባንኩ አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ123.5986 ብር እየገዛ በ126.0706 ብር እየሸጠ መሆኑን አስታውቋል።
ዳሽን ባንክ ከ29 ቀናት በፊት ያወጣውን ተመን አስቀጥሎ አንድ ዶላርን በ124.7171 ብር እየገዛ በ127.2114 ብር እየሸጠ መሆኑን ገልጿል።
አቢሲኒያ ባንክ በውጭ ምንዛሬ ተመኑ ላይ መጠነኛ የሳንቲም ጭማሪ አድርጎ አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ124.7290 ብር ገዝቶ በ127.2236 ብር እየሸጠ ነው።
ብርሃን ባንክ የምንዛሬ ተመኑ ላይ መጠነኛ የሳንቲም ጭማሪ አድርጓል። በዚህም አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ124.8050 ብር ገዝቶ በ127.3011 ብር እየሸጠ መሆኑን አስታውቋል።
ጸደይ ባንክም የታህሳስ 15 የውጭ ምንዛሬ ተመኑ ላይ መጠነኛ ጭማሪ አድርጎ አንድ ዶላርን በ124.8438 ብር እየገዛ በ127.3407 ብር እየሸጠ መሆኑን ነው የገለጸው።