የተሰናባቹ የባይደን አስተዳደር ለታይዋን የ571 ሚሊየን ዶላር ወታደራዊ ድጋፍ ፈቅዷል
አሜሪካ ለታይዋን ተጨማሪ የወታደራዊ ድጋፍ እና ሽያጭ ይፋ ማድረጓን ተከትሎ ቤጂንግ ዋሽንግተንን በእሳት እየተጫወተች ነው ስትል አስጠንቅቃለች።
የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ትናንት ባወጣው መግለጫ፤ አሜሪካ በታይዋን ሰርጥ ውስጥ የምታካሂደውን ሰላምና መረጋጋትን የሚጎዱ አደገኛ እንቅቃሴዎች እንድታቆም አሳስቧል።
የዋይት ሃውስ ባሳለፍነው አርብ ባወጣው መግለጫው የተሰናባቹ የፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አስተዳደር ለታይዋን የ571.3 ሚሊየን ዶላር ወታደራዊ ድጋፍ መፍቀዱን አስታውቋል።
የዋይት ሀውስ መግለጫ ስለ ወታደራዊ ድጋፉ ዝርዝር ጉዳዮችን ባይሰጥም፣ አሜሪካ ለታይዋን ተደራዊ ድጋፍ ስትፈቅድ ከሶስት ወር ባነሰ ጊዝ ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ ነው።
ቻይና ከወራት በፊት ለታይዋን የ567ሚ ዶላር ወታደራዊ ድጋፍ ይፋ ማድረጓ ይታወሳል።
የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር “ይህ እርምጃ የቻይናን ሉዓላዊነት እና የደህንነት ጥቅሞችን በእጅጉ ይጥሳል” ያለ ሲሆን እንዲህ አይነቱን ተግባር በጽኑ እንደሚቃወምም አስታውቋል።
የቻይና የታይዋን ጉዳይ ፅህፈት ቤት በጉዳዩ ላይ በሰጠው መግለጫ፤ አሜሪካ የጦር መሳሪያ ድጋፍ እርምጃ መሪዎቿ የታይዋንን አጻ ሀገርነት አንደግፍም የሚለውን አቋም የሚቃረን ነው ብለዋል።
አሜሪካ ለታይዋን የምታደርገውን የመሳሪያ ድጋፍ በአስቸኳይ እንድታቁምና የታይዋንን ጉዳይ በከፍተኛ ጥንቃቄ እንትይዘው የጽህፈት ቤቱ ቃል አቀባይ ዝሁ ፍሪንግሊያን አስታውቀዋል።
ቤጂንግ የሉአላዊ ግዛቴ አካል ናት የምትላት ታይፒ እንደ ሉአላዊ ሀገር ከሌሎች ሀገራት ጋር መሰል ስምምነት መፈራረም እንደማትችል ደጋግማ ማሳሰቧ ይታወሳል።
ታይፒ ግን ባለፉት ሶስት አመታት በተለይ ከአሜሪካ ጋር ወዳጅነቷን አጥብቃ የጦር መሳሪያ ሽያጭ ስምምነቶችንም ፈጽማለች።
ይህ በጦር መሳሪያ ሽያጭ የሚታይ የዋሽንግተን ጣልቃገብነት የቤጂንግን ወታደራዊ ዝግጁነት እያጠናከረው ስለመምጣቱም ነው የሚነገረው።
በየእለቱ በታይዋን ሰርጥ አካባቢ ቅኝት የሚያደርጉ የቻይና አውሮፕላኖች ቁጥር እየጨመረ መሄዱም ውጥረቱን አንሮታል።