በታህሳስ 22 የባንኮች የውጭ ምንዛሬ ተመን የዶላር ዋጋ ስንት ደረሰ?
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አንድ ዶላርን በ124 ብር ገዝቶ በ127 ብር እንደሚሸጥ አስታውቋል
የግል ንግድ ባንኮች ለአንድ ዶላር ከ124 ብር ጀምሮ የመግዣ ዋጋ አቅርበዋል
ኢትዮጵያ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርአት ተግባራዊ እንዲደረግ መወሰኗን ተከትሎ ባንኮች በየእለቱ የውጭ ምንዛሬ ተመን ይፋ ማድረጋቸውን ቀጥለዋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዛሬ ታህሳስ 22 ቀን 2017 ዓ.ም የውጭ ሀገር ገንዘቦችን የሚገዛበትን እና የሚሸጥበትን ተመን ይፋ ሲያደርግ የባለፈውን ሳምንት ዋጋ አስቀጥሏል። ባንኩ አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ123.5986 ብር እየገዛ በ126.0706 ብር እየሸጠ መሆኑን አስታውቋል።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከትናንቱ የምንዛሬ ተመን መጠነኛ ጭማሪ አድርጎ አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ124.7128 ብር እየገዛ በ127.2071 ብር እየሸጠ እንደሚገኝ ገልጿል።
ዳሽን ባንክ ከአንድ ወር በፊት በፊት ያወጣውን ተመን ያስቀጠለ ሲሆን አንድ ዶላርን በ124.7171 ብር በመግዛት በ127.2114 ብር እየሸጠ ይገኛል።
አቢሲኒያ ባንክ ከአምስት ቀናት በፊት ያወጣውን የምንዛሬ ተመን አስቀጥሏል። በዚህም አንድ ዶላርን በ124.7045 ብር እየሸጠ በ127.1986 ብር እየሸጠ ነው።
ብርሃን ባንክ የምንዛሬ ተመኑ ላይ መጠነኛ የሳንቲም ጭማሪ አድርጎ አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ124.8080 ብር ገዝቶ በ127.3042 ብር እየሸጠ መሆኑን አስታውቋል።