ኪም ለፑቲን በጻፉት ደብዳቤ ከሩሲያ ጋር ያላቸውን ግንኙነት የበለጠ እንደሚያጠናክሩ ቃል ገቡ
ባለፈው ሐምሌ ወር ኪም እና ፑቲን ከሁለቱ አንደኛቸው በሚጠቁበት ወቅት እርስበርስ ወታደራዊ ድጋፍ ለማድረግ የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራርመዋል
ሰሜን ኮሪያ በዩክሬኑ ጦርነት ከሩሲያ ጎን ተሰልፈው የሚዋጉ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮችን ማሰማራቷን ዩክሬን እና ዋሽንግተን ገልጸዋል
ኪም ለፑቲን በጻፉት ደብዳቤ ከሩሲያ ጋር ያላቸውን ግንኙነት የበለጠ እንደሚያጠናክሩ ቃል ገቡ።
የሰሜን ኮሪያው ፕሬዝደንት ኪም ጆንግ ኡን ሀገራቸው ከሩሲያ ጋር ያላትን ሁሉን አቀፍ ግንኙነት እንደምታጠናክር ለሩሲያው ፕሬዝደንት ፑቲን ሰኞ እለት በጻፉት ደብደቤ ቃል መግባታቸውን ሮይተርስ ኬሲኤንኤን ጠቄሶ ዘግቧል።
ፑቲን በደብዳቤያቸው ለፑቲን እና ለሁሉም ሩሲያውያን የአዲስ አመት ሰላምታ ማቅረባቸውን እና ሁለቱ መሪዎች በዚህ አመት የጀመሩትን የሁለትዮሽ ግንኙነት ከፍተኛ ደረጃ ለማድረስ እንደሚፈልጉ መግለጻቸውን ዘገባው ጠቅሷል።
ኪም "አዲሱ 2025 የሩሲያ ጦር እና ህዝብ ኒዮ-ናዚዝምን የሚያሸንፉበት በ21ኛው ክፍለ ዘመን የመጀመሪያው አመት ሆኖ እንዲመዘገብ ተመኝተዋል።"
ባለፈው ሐምሌ ወር ኪም እና ፑቲን ከሁለቱ አንደኛቸው በሚጠቁበት ወቅት እርስበርስ ወታደራዊ ድጋፍ ለማድረግ የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራርመዋል።
ስምምነቱ ህግ እንዲሆን ሁለቱም ሀገራት አጽድቀውታል።
ሰሜን ኮሪያ በዩክሬኑ ጦርነት ከሩሲያ ጎን ተሰልፈው የሚዋጉ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮችን ማሰማራቷን ዩክሬን እና ዋሽንግተን ገልጸዋል።