በጥቅምት 19 የባንኮች የውጭ ምንዛሬ ተመን የአንድ ዶላር ዋጋ ስንት ብር ገባ?
የግል ንግድ ባንኮች ለ1 ዶላር ከ118 እስከ 121 ብር መግዣ፤ ከ119 እስከ 123 ብር መሸጫ ዋጋ አውጥተዋል
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከትናንት ዋጋው 3 ብር ገደማ በመጨመር አንድ ዶላርን በ119 ብር እየገዛ፤ በ121 ብር እሸጠ ይገኛል
ኢትዮጵያ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርአት ተግባራዊ እንዲደረግ መወሰኗን ተከትሎ ባንኮች በየእለቱ የውጭ ምንዛሬ ተመን ይፋ ማድረጋቸውን ቀጥለዋል።
ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ መግዣና መሸጫ መሃል ያለው ልዩነት እንዲቀራረብ ባሳሰበ ማግስት የውጭ ምንዛሬ ተመን ላይ ለውጥ ታይቷል።
ባንኮች በውጭ ምንዛሬ መሸጫ ዋጋቸው ላይ ካደረጉት ቅናሽ ባሻገር በመግዣ ዋጋቸውም ላይ ከ10 ብር በላይ ጭማሪ አድርገዋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዛሬ ጥቅምት 19 2017 ዓ.ም የውጭ ሀገር ገንዘቦችን የሚገዛበትን እና የሚሸጥበትን ዋጋ ይፋ ሲያደርግ ትናነት ሲሸጥ ከነበረበት ዋጋ ላይ የ3 ብር ገደማ ጭማሪ አድርጓል።
በዚህም አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ119.2044 ብር እየገዛ ሲሆን፤ በ121.5885 ብር እየሸጠ መሆኑን አስታውቋል።
ኦሮሚያ ባንክ ዛሬም ከፍተኛውን የዶላር መግዣ ዋጋ አቅርቧል። ባንኩ የጥቅምት 19 2017 ዓ.ም እለታዊ የምንዛሬ ተመኑን ይፋ ሲያደርግ የሰሞኑን ዋጋ አስቀጥሎ አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ121.3066 ብር እየገዛ በ123.7327 ብር እየሸጠ ይገኛል።
አንበሳ ባንክም ከፍተኛ የምንዛሬ ዋጋ ካቀረቡት ውስጥ ሲሆን፤ ባንኩ የጥቅምት 18 2017 ዓ.ም እለታዊ የምንዛሬ ተመኑም አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ120.0892 ብር እየገዛ በ122.4910 ብር እየሸጠ ይገኛል።
ንብ ባንክ እለታዊ የውጭ ምንዛሬ ተመኑን ይፋ አድርጓል። በዚህም አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ118.3217 ብር ገዝቶ በ120.6882 ብር እየሸጠ መሆኑን ነው ያስታወቀው።
ዳሽን ባንክም የጥቅምት 19 2017 ዓ.ም እለታዊ የምንዛሬ ተመኑን ይፋ ሲያደርግ የሰሞኑን ዋጋ አስቀጥሎ አንድ ዶላርን በ119.2255 ብር እየገዛ መሆኑን ገልጿል። 121.6100 ብር የባንኩ የዶላር መሸጫ ዋጋ ነው።