በፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የተመረጡ የክሪፕቶ መገበያያዎች ምን ምን ናቸው?
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አምስት የክሪፕቶ ከረንሲዎችን ዝርዝር ይፋ አድርገዋል

አሜሪካ በቅርቡ ዓለም አቀፍ የክሪፕቶ ግብይት ጉባኤ እንደምታዘጋጅ ተገልጿል
በፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የተመረጡ የክሪፕቶ መገበያያዎች ምን ምን ናቸው?
“ቢትኮይን የአጭበርባሪዎች ነው” በማለት የሚታወቁት ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አሁን ላይ ዋነኛ የክሪፕቶ ከረንሲ ወይም ምናባዊ ግብይት አቀንቃኝ ሆነዋል፡፡
ከሰሞኑ ደግሞ የአሜሪካ እና የዓለም ክሪፕቶ መገበያያ እና ሀብት መያዣ ይሆናሉ ያሏቸውን ዘርዝረዋል፡፡
ፕሬዝዳንት ትራምፕ አምስት የክሪፕቶ ከረንሲ መገበያያዎችን ዝርዝር ይፋ ያደረጉ ሲሆን ከነዚህ ውስጥም ቢትኮይን፣ ኢቴሪየም፣ኤክስአርኤን፣ሶላና እና ካርዳኖ ዋነኞቹ ናቸው፡፡
ፕሬዝዳንቱ የወደፊቱ የዓለም ክሪፕቶከረንሲ መገበያያ ብለው ስማቸውን ከጠቀሱ በኋላ የኩባንያዎቹ አክስዮን ዋጋ እስከ 60 በመቶ ጭማሪ አሳይተዋል፡፡
የአሜሪካን የመጠባበቂያ ገንዘብን በነዚህ መገበያያ ገንዘቦች ሊያስቀምጡ እንደሚችሉ ፍንጭ የሰጡት ፕሬዝዳንቱ በቅርቡም በነጩ ቤተ መንግስት የክሪፕቶ ከረንሲ ጉባኤ እንደሚያዘጋጁም ተናግረዋል፡፡
አሁን ላይ አንድ ቢትኮይን 91 ሺህ ዶላር በመሸጥ ላይ ሲሆን ላለፉት ቀናት ቅናሽ ካሳየ በኋላ መጠነኛ ማንሰራራት አሳይቷል፡፡
እንደ ክሪፕቶ ከረንሲ ባለሙያዎች መረጃ ከሆነ በ2025 ደግሞ የአንድ ቢትኮይን ዋጋ ወደ 150 ሺህ ዶላር ያድጋል የተባለ ሲሆን በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት ውስጥ ደግሞ ወደ አንድ ሚሊዮን ዶላር እንደሚያድግ ባለሙያዎች ተናግረዋል፡፡
ትራምፕ የቀድሞ የፔይፓል ክፍያ ስራ አስኪያጅ እና የክሪፕቶ ከረንሲ ግብይት ደጋፊ የሆኑት ዴቪድ ሳክስን የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ እና ክሪፕቶ ጉዳዮች ሀላፊ አድርገው መሾማቸው ይታወሳል፡፡