የአሜሪካ ቀዳሚያ እመቤት ሜላኒያ ትራምፕ አዲስ ክሪፕቶከረንሲ አስተዋወቁ
የዶናልድ ትራምፕ ባለቤት የሆኑት ሜላኒያ ትራምፕ አዲስ ክሪፕቶከረንሲ ይፋ አድርገዋል
አዲሱ የሜላኒያ ክሪፕቶ በአንድ ቀው ውስጥ የ1 ነጥብ 7 ቢሊዮን ዶላር ግብይት አድርጓል
የአሜሪካ ቀዳሚያ እመቤት ሜላኒያ ትራምፕ አዲስ ክሪፕቶከረንሲ አስተዋወቁ።
47ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ሆነው ዛሬ ስራ የሚጀምሩት ዶናልድ ትራምፕ ስልጣን ከመረከባቸው አንድ ቀን በፊት "ትርምፕ ዶላር" የተሰኘ ክሪፕቶከረንሲ ለገበያ አስተዋውቀዋል።
እንዲሁም የዶናልድ ትራምፕ ባለቤት ሜላኒያ ትራምፕ ከባላቸው አንድ ቀን ዘግይተው "ሜላኒያ ዶላር" የተሰኘ ክሪፕቶከረንሲ ለገበያ አቅርበዋል።
ሜላኒያ ዶላር እስካሁን የ1 ነጥብ 7 ቢሊዮን ዶላር ግብይት ያደረገ ሲሆን የባለቤታቸው ትራምፕ ዶላር ደግሞ የ12 ቢሊዮን ዶላር ሽያጭ ወከናውኗል።
ከሶስት ዓመት በፊት ቢትኮይን እና መሰል የክሪፕቶከረንሲ ግብይቶች ማጭበርበሪያ መንገዶች ናቸው ሲሉ የነበሩት ዶናልድ ትራምፕ አሁን ላይ ዋነኛ ደጋፊ እና ተዋናይ ሆነዋል።
አሁን ላይ አንድ ቢትኮይን በ140 ሺህ ዶላር እየተሸጠ ሲሆን ዶናልድ ትራምፕ ስልጣን ከቱረከቡ በኋላ ዋጋው እየጨመረ እንደሚሄድ ይጠበቃል።
አሜሪካንን ዋነኛ የክሪፕቶ ከረንሲ መገበያያ ማዕከል አደርጋለሁ የሚሉት ዶናልድ ትራምፕ ቤተሰባቸውን በዚህ ኢንቨስትመንት መስክ አሰማርተዋል።
አሜሪካ የክሪፕቶከረንሲ ማዕከል እንድትሆን ፖሊስ፣ መሰረተ ልማት እና ሌሎች አስፈላጊ አሰራሮችን እንደሚያሻሽሉም ቃል ገብተዋል።
የዶናልድ ትራምፕ የበኩር ልጅ የሆነው ኤሪክ ትራምፕ የአንድ ቢትኮይን ዋጋ በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት ውስጥ አንድ ሚሊዮን ይደርሳል ማለቱ ይታወሳል።