የዲጂታል ገንዘብ የሆነው ክሪፕቶከረንሲ ምንድን ነው? እንዴትስ ይሰራል?
ከወረቀትና የሳንቲም ገንዘብ በተጨማሪ የዲጂታል ገንዘቦች የክፍያና ኢንቨስትመንት አማራጭ እየሆኑ መጥተዋል
አንዳንድ ሰዎች እና ተቋማት ክሪፕቶ በመባል የሚታወቀውን የክፍያ አማራጭ በመጠቀም ግብይቶችን ያካሂዳሉ
የዲጂታል ገንዘብ የሆነው ክሪፕቶከረንሲ ከወረቀትና የሳንቲም ገንዘብ በተጨማሪ አሁን ላይ ሌላኛው ለግዢ እና ኢንቨስትመንት ጥቅም ላይ የሚውል ገንዘብ እየሆነ መጥቷል።
አንዳንድ ተቋማትና እና ግለሰቦች አሁን ላይ የፋይናንስ ክፍያዎችን ክሪፕሮከረንሲ በመባል የሚታወቀውን የዲጂታል ገንዘብ በመጠቀም እየፈጸሙ እንደሆነም ነው የሚነገረው።
የዲጂታል ገንዘብ የሆነው ክሪፕቶከረንሲ ምንድን ነው?
በብዙሃን ዘንድ ክሪፕቶ ተብሎ የሚጠራው ክሪፕቶከረንሲ ዲጂታል ገንዘብ ወይም ምናባዊ ገንዘብ በሚል ልንጠራው እንችላለን።
ክሪፕቶከረንሲ የማይታይ፣ የማይጨበጥ እና አካል ገልጦ የማይከሰት ዋጋ ያለው የገንዘብ ዓይነት ሲሆን፤ በድረ ገጽ አማካኝነት ሰዎች ምንም ማዕከላዊ የባንክ ስርዓት ሳይኖር ልውውጥ የሚያደርጉበት እና ለግብይት አገልግሎት የሚውል ነው።
ክሪፕቶ እንደዚህ አይነት ክፍያዎችን በሚቀበሉ ተቋማት ውስጥ የዕለት ተዕለት ሸቀጦችን ለመግዛት ወይም የኢንቨስትመንት ለመክፈል ጥቅም ላይ የሚውል ነው።
አሁን ላይ ከ20 ሺህ በላይ የምናባዊ ገንዘብ ዓይነቶች ያሉ ሲሆን በምንዛሬ ደረጃ ቁንጮ ላይ የሚቀመጠው ቢትኮይን የሚባለው የክሪፕቶ ከረንሲ ነው።
ክሪፕቶካረንሲ እንዴት ይሰራል?
ክሪፕቶከረንሲ ግብይቶችና የገንዘብ ዝውውሮች የሚከናወኑት ብሎክቼይን በሚባል ቴክኖሎጂ ነው። ብሎክቼይን የተባለው ይህ ፋውንዴሽን ማጭበርበርን ለመከላከል እና የሚከናወኑ ግብይቶች መዝግቦ ለመያዝ የሚያስችል ዲጂታል መከላከያ ነው።
በተለምዶ የክሪፕቶ ገንዘብ በብሎክቼይን ላይ በአንድ የተወሰነ ኩባንያ በተፈጠሩ ሳንቲሞች ወይም ቶከኖች መልክ ነው የሚመጣው።
እነዚህ ሳንቲሞች ብዙውን ጊዜ የጋራ ምንዛሪ እንዳላቸው ገንዘቦች በአካላዊ መልክ ሳይገሆን በዲጂታል መልክ ብቻ የሚቀርቡ ናቸው።
የክሪፕቶ ገንዘብን እንዴት መግዛት ይቻላል?
የዲጂታል ገንዘብ የሆነው ክሪፕቶከረንሲ የተለያዩ አማራጮችን በመጠቀም መግዛት የሚቻል ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ፤
ለውውጦች
የክሪፕቶ ልውውጦች ዲጂታል ገንዘብን ለመገበያየት ያገለግላሉ። የክሪፕቶ ልውውጦች ውስጥ አብዛኛውን ጊዜ አንድ ዓይነት ክሪፕቶ ለሌላ ክሪፕቶ ወይም ከክሪፕቶ ወደ ወረቀት ምንዛሪ ያካትታል።
የክፍያ መተግበሪያዎች
እንደ ፔይፓል (PayPal) ያሉ መደበኛ የክፍያ መተግበሪያዎች ግብይቶችን ለመፈጸም ክሪፕቶንን ለመጠቀም አማራጭ ይሰጡናል።
ኤቲኤም (ATM)
እንደ ቢትኮይን ያሉ ታዋቂ እና ግዙፍ የክሪፕቶ ፕትላፎርሞች ልዩ የሆኑ ኤቲኤም በማቆም የክሪፕቶ ሳንቲሞችን ወደ ካሽ ለውጠን እንድናወጣ እንዲሁም የባንክ ካርዳችንን ተጠቅመን ክሪፕቶ ገንዘቦችን እንደንገዛ አማራጭ አላቸው።
የክሪፕቶ ገንዘብ ደህንነቱ ምን ያክል የተጠበቀ ነው?
ክሪፕቶ ላይ ያሉት ቡድኖች የብሎክቼይን ቴክኖሎጂ የበለጠ ደህንነትን እንደሚሰጥ እና ንብረቶቻችዎን በተሻለ ሁኔታ እንደሚጠብቅ ያምናሉ።
የክሪፕቶ ገንዘብ ስጋቶች?
የክሪፕቶ በአንፃራዊነት አዲስ እና በየጊዜው እያደገ ያለ ኢንዱስትሪ በመሆኑ የራሱ ተስፋ እና ስጋቶች አሉት። ዛሬ ጥሩ ውጤት የሚያስገኙ ኢንቨስትመንቶች ነገ ወደ ተመሳሳይ ውጤት ሊያገኙ አይችሉም።
ኢትዮጵያ ቢትኮይንን መሰል የዲጂታል መገበያያ ገንዘቦችን ወይም ክሪፕቶከረንሲዎችን ከሁለት ዓመት በፊት ምገዷ ይታወሳል።
የኢትዮጰያ ብሔራዊ ባንክ በወቅቱ ባወጣው መግለጫ “ከህግ እውቅና ውጪ እንደ ቢትኮይን እና የመሳሰሉት የክሪፕቶ ከረንሲ ዲጂታል መገበያያ ገንዘብ አገልግሎት በኢትዮጵያ እየተስፋፋ መምጣቱን በጥናት ደርሼበታለሁ ብሏል።
"ምናባዊ ንብረትን ወይም ዲጂታል መገበያያ ገንዘብ" ለግብይት ወይም ለክፍያ መጠቀም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዕውቅና ያልተሰጠው ድርጊት በመሆኑ ህብረተሰቡ ከእንደዚህ አይነት ሕገ-ወጥ ተግባር እራሱን እንዲጠብቅ ባንኩ ማሳሰቡ ይታወሳል።