ዶናልድ ትራምፕ ተጨማሪ ሹመቶችን ለማን እንደሚሰጡ ፍንጭ ሰጡ
ህገወጥ ስደተኞችን ወደ መጡበት የመመለስ ስራውን የሚያስተባብረው ተቋም ቶም ሆማንን እንደሚሾሙ ይፋ አድርገዋል
የኒዮርኳ ኤሊዝ ስቴፋኒክ በተመድ የአሜሪካ አምባሳደር ተደርገው እንደሚሾሙ እና እንደተቀበሉ ተናግረዋል
ዶናልድ ትራምፕ ተጨማሪ ሹመቶችን ለማን እንደሚሰጡ ፍንጭ ሰጡ፡፡
ባሳለፍነው ሳምንት የተደረገው የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ጉዳይ አሁንም ዓለምን ትኩረት መሳቡን ቀጥሏል፡፡
ከምርጫው ውጤት መታወቅ በኋላ አሸናፊው ዶናልድ ትራምፕ በሚመሰርቱት ካቢኔ ውስጥ እነማንን ሊያካትቱ ይችላሉ የሚለው ጉዳይ የሚዲያዎች ዋነኛ ትኩረት ሆኗል፡፡
ዶናልድ ትራምፕ ጥር ወር ላይ ከተሰናባቹ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በይፋ ስልጣን የሚረከቡ ሲሆን ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር እንዲኖት ጥረቶች በመካሄድ ላይ ናቸው ተብሏል፡፡
በተለይም ዶናልድ ትራምፕ ቁልፍ በሚባሉ የመንግስታቸው ሀላፊነት ቦታዎች ላይ የሚያደርጓቸው ሹመቶች ተጠባቂ ሲሆኑ ተመራጩ ፕሬዝዳንትም እነማንን እንደሚሾሙ በመናገር ለይ ናቸው፡፡
የስደተኞች ጉዳይ በምርጫ ቅስቀሳ ወቅት ዋነኛ አጀንዳ የነበረ ሲሆን በተለይም የመኖሪያ ፈቃድ እና የጉዞ ሰነድ የሌላቸው ዜጎችን ወደመጡበት ሀገር አባርራለሁ ሲሉ ቃል መግባታቸውም ይታወሳል፡፡
ትራምፕ እና ፑቲን በስልክ ተወያዩ የሚለው መረጃ ሀሰት ነው ሲል ክሬሚሊን አስተባበለ
ዶናልድ ትራምፕ ትሩዝ ሶሻል በተሰኘው የማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ በስደተኞች ላይ የከረረ አቋም አላቸው የሚባሉት ቶም ሆማን የሀገር ውስጥ ደህንነት ሃላፊ እንደሚሆኑ አሳውቀዋል፡፡
አዲሱ የዶናልድ ትራምፕ አስተዳድር በሚሊዮን የሚቆጠሩ ህገወጥ ስደተኞችን ወደ መጡበት ሀገር በሀይል ሊያባርር እንደሚችል ተገልጿል፡፡
እንዲሁም የኒየፐርክ ሴናተሯ ኤሊዝ ስቴፋኒክ በተመድ የአሜሪካ አምባሳደር ተደርገው እንደሚሾሙ የተናገሩ ሲሆን ኤሊዝ ሹመቱን በደስታ እንደተቀበሉ መናገራቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
ዶናልድ ትራምፕ የቴስላ ኩባንያ መስራቹን ኢለን መስክ፣ የግል ተወዳዳሪ የነበሩት ኬኔዲ ጁኒየር እና ሉሎች ተጽዕኖ ፈጣሪዎችን በመንግስታቸው ውስጥ ሃላፊነት ይኖራቸዋል ብለዋል፡፡
ይህ በዚህ እንዳለ ግን በቀድሞ መንገስታቸው ስር ቁልፍ አጋራቸው የነበሩት ኒኪ ሀሌይ እና ማይክ ፖምፒዮን በአዲሱ መንግስታቸው ላይ እንደማያካትቱ ተናግረዋል፡፡
ደናልድ ትራምፕ በሁለቱም ምክር ቤቶች ያሉ አብላጫ ወንበሮችን መያዛቸው ፖሊሲዎቻቸውን ያለ ዲሞክራቶች ጣልቃ ገብነት እንዲያስፈጽሙ ይረዳቸዋልም ተብሏል፡፡