የዲ.አር ኮንጎ ፕሬዝዳንት የሩዋንዳ አቻቸው ካጋሜን ከሂትለር ጋር ማመሳሰላቸው አነጋጋሪ ሆኗል
ፕሬዝዳንት ቲሺሴኬዲ “ፖል ካጋሜ ከሂትለር ጋር ተመሳሳይ የሆነ ባህሪ እያሳየ ነው ብለዋል
"የፖል ካጋሜ መጨረሻ እንደ ሂትለር እንደሚሆን ቃል እገባለሁ" ሲሉ ፕሬዝዳንት ቲሺሴኬዲ ተናግረዋል
የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፕሬዝዳንት ፌሊክስ ቲሺሴኬዲ የሩዋንዳ አቻቸው ፖል ካጋሜን ከሂትለር ጋር አወዳድረዋል።
ፌሊክስ ቲሺሴኬዲ በሩዋንዳ በሩዋንዳ ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜን ከአዶልፍ ሂትለር ጋር በማወዳደር የሰነዘሩ የቃላጥ ጥቃት በሁለቱ መሪዎች መካከል ያለውን ፍጥጫ ወደ ሌላ ደረጃ ከፍ ብሏል።
ፕሬዝዳንት ፌሊክስ ቲሺሴኬዲ በንግግራቸው አክለውም “ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ እንደ አዶለፍ ሂትለር እያደረገው ነው”፤ መጨረሻ እንደ ሂትለር እንደሚሆን ቃል እገባለሁ" ብለዋል።
ድጋሚ ለመመረጥ በምርጫ ቅስቀሳ እያደረገ ያሉት ፕሬዝዳንት ቲሺሴኬዲ፤ በሩዋንዳ ድንበር አቅራቢያ በቡካቩ በተካሄደው ሰልፍ ላይ ንግግር ባደረጉበት ነው የሩዋንዳ አቻቸው ላይ የቃላት ጥቃት የሰነዘሩት።
ፕሬዝዳንት ፌሊክስ ቲሺሴኬዲ በቱትሲ የሚመሩ ኤም 23 አማፂያንን ጨምሮ በርካታ ታጣቂ ቡድኖች በሀገራቸው ሁከትና ብጥብጥ መፍጠራቸውን በመግለጽ፣ ታጣቂዎቹ በሩዋንዳ እንደሚደገፉ ተናግሯል።
ፕሬዝዳንት ቲሺሴኬዲ፤ ሩዋንዳ በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ምሥራቃዊ ክፍል ያሉትን አማፂያን ትደግፋለች በማለት በተደጋጋሚ ወቀሳ የሚያቀርቡ ሲሆን፤ ሩዋንዳም ክሱን በተደጋጋሚ ስታስተባብልና ውድቅ ስታደረግ ቆይታለች።
የሩዋንዳ መንግስት ቃል አቀባይ የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፕሬዝዳንት አስተያየት "ከፍተኛ ውንጀላ እና ግልጽ የሆነ ስጋት" ሲሉ ገልፀውታል።