ዶ/ር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ወደ ጣሊያን አቅንተው በግድቡ ዙሪያ መምከራቸውን ገለጹ
ዶ/ር ኢንጂነር ስለሺ በውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትርነት አገልግለዋል
ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ የድንበር ተሻጋሪ ወንዞችና የህዳሴ ግድብ ዋና ተደራዳሪና አማካሪ ሆነው ተሾመዋል
የቀድሞው የወሃ፣መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር የነበሩት ዶ/ር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ በፌስቡክ ገጻቸው ባሰፈሩት መልእክት ዛሬው እለት በጣሊያን ሀገር በግድቡ ዙሪያ ምክክር ማድረጋቸውን ተናግረዋል፡፡
ዶ/ር ኢንጂነር ስለሺ ከጣሊያን ምክትል የውጭ ጉዳይና ትብብር ሚኒስትር ማሪያ ሰረኒ ጋር በወቅታዊ የኢትዮጵያ ሁኔታና በህዳሴው ግድብ ዙሪያ መምከራቸውን ገልጸዋል፡፡
ዶ/ር ኢንጂነር ስለሺ በነገው እለት በጣሊያን በሚካሄደው የአፍሪካ ስብሰባ ላይ እንደሚካፈሉ ተናግረዋል፡፡
- “በቀጣይ ሀገሬ በምትፈልገኝ አገልግሎት የምሰማራ ይሆናል”- ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ
- ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ የድንበር ተሻጋሪ ወንዞችና የህዳሴ ግድብ ዋና ተደራዳሪና አማካሪ ሆነው ተሸሙ
የቀድሞው የውሃና፣ መስኖና ኢነርጅ ሚኒስትር የነበሩት ዶ/ር ኢንጂነር ስለሲ በቀለ በትንናትናው የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ካቢኔ ውስጥ አልተካተቱም ነበር፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በዛሬው እለት ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለን የድንበር ተሻጋሪ ወንዞችና የህዳሴ ግድብ ዋና ተደራዳሪና አማካሪ አድርገው ሾመዋቸዋል፡፡
ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በተጨማሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለከፍተኛ የመንግስት ሃላፊነት ቦታዎች የተለያዩ ሾመቶችን ሰጥተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በዛሬው ሹመታቸው የቀድሞ የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለን በሚኒስትር ማዕረግ የድንበር ተሻጋሪ ወንዞችና የህዳሴግድብ ዋና ተደራዳሪና አማካሪ አድርገው ሾመዋል።
የቀድሞው የውሃና፣ መስኖና ኢነርጅ ሚኒስትር የነበሩት ዶ/ር ኢንጂነር ስለሲ በቀለ በትንናትናው የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ካቢኔ ውስጥ አልተካተቱም ነበር፡፡
ዶ/ር ኢንጂነር ስለሺ በህዳሴው ግድብ የሶስትዮሽ ድርድር ላይ የኢትዮጵያ የተደራዳሪ ቡድን ሲመሩ ቆይተዋል፡፡