ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ የድንበር ተሻጋሪ ወንዞችና የህዳሴ ግድብ ዋና ተደራዳሪና አማካሪ ሆነው ተሸሙ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለከፍተኛ የመንግስት ሃላፊነት ቦታዎች የተለያዩ ሾመቶችን ሰጥተዋል
ዶክተር ለገሰ ቱሉ ደግሞ በሚኒስትር ማዕረግ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ኃላፊ ሆነው ተሸመዋል
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለከፍተኛ የመንግስት ሃላፊነት ቦታዎች የተለያዩ ሾመቶችን ሰጥተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በዛሬው ሹመታቸው የቀድሞ የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለን በሚኒስትር ማዕረግ የድንበር ተሻጋሪ ወንዞችና የህዳሴግድብ ዋና ተደራዳሪና አማካሪ አድርገው ሾመዋል።
በተጨማሪም አቶ ተፈሪ ፍቅሬን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ሃላፊ እና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር አድርገው በድጋሚ መሾማቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ያለገነው መረጃ ያመለክታል።
የቀድሞ የፌሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አቶ አደም ፋራህ ም በሚኒስትር ማዕረግ የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ዋና አስተባባሪ ሆነው ተሹመዋል።
አቶ ተስፋዬ ቤልጅጌ በሚኒስትር ማዕረግ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ተጠሪ ሆነው ሲሾሙ፤ ዶክተር ለገሰ ቱሉ ደግሞ በሚኒስትር ማዕረግ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ኃላፊ ሆነው ተሸመዋል።
ዶክተር ምህረት ደበበ የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ፕሬዝዳንት ኢኒዲሆኑ ተሸመዋል።
አቶ ፍሰሃ ይታገሱ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ እንዲሁም አቶ አብዱራህማን ሩቤ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሆነው መሾማቸውን ጽህፈት ቤቱ አስታውቋል።