ዶ/ር ሱልጣን አልጃብር የኮፕ 28 ፕሬዝዳንትነት ስፍራን ተረከቡ
የኮፕ27 ፕሬዝዳነት የነበሩት ሰሚ ሹክሪ ስፍራውን ለዶ/ር ሱልጣን አልጃብር አስረክበዋል
የ28ኛው የተባበሩት መንግስታቱ ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ በዱባይ እየተካሄደ ነው
ዶ/ር ሱልጣን አልጃብር የ2023 የአለም የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ 28) ፕሬዝዳንትነት ስፍራን በይፋ ተረክበዋል።
የ28ኛው የተባበሩት መንግስታቱ ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ (ኮፕ28) በዛሬው እለት በአረብ ኢምሬትስ መካሄድ ጀምሯል።
በጉባዔው የመጀመሪያ መክፈቻ ቀን ላይም የ27ኛው የተባበሩት መንግስታቱ ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ ፕሬዝዳንት ስፍራውን ለተከታዩ አስረክበዋል።
- ዶክተር ሱልጣን አልጃቢር የኮፕ28 ጉባኤ ትክክለኛው መሪ መሆናቸው ተገለጸ
- ሱልጣን አል ጀባር በታይም መጽሄት የአየር ንብረት ተጽእኖ ፈጣሪ ሰዎች ዝርዝር ውስጥ ተካተቱ
በዚህም የ27ኛው የተባበሩት መንግስታቱ ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ (ኮፕ 27) ፕሬዝዳንት የግብጹ የውጭ ጉዳይ ሳሚ ሹክሪ ኃለፊነጹን ለኮፕ 28 ፕሬዝዳንተ አስረክበዋል።
በዚህም የአረብ ኤምሬትስ የንግድ እና የቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር ሱልጣን አልጃበር የ28ኛው የተባበሩት መንግስታቱ ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ (ኮፕ28) ስፍራን በይፋ ተረክበዋል።
ዶ/ር ሱልጣን በርክክቡ ወቅት ባደረጉት ንግገር ሁሉንም ተሳታፊወች ያመሰገኑ ሲሆን፤ የዘንድሮ ጉባዔ ትልቁ አጀንዳ ፋይናንስ ነው ብለዋል።
የአረብ ኤምሬትስ የንግድ እና የቴክኖሎጂ ሚኒስትር ሆነው ያገለገሉት ሱልጣን ቢን አህመድ፥ በከየር ነብረት ለውጥ ዙሪያ በሚከናወኑ ስራዎች ስማቸው ከፊት ይነሳል።
ሁለት ጊዜ ሀገራቸውን በአለም አቀፉ የአየር ንብረት ጉባኤ ወክለው የቀረቡት ሰው ከ10 በላይ መሰል አለማቀፍ ጉባኤዎች ላይ ያቀረቧቸው ሀሳቦችም የብስለታቸውን ደረጃ ስለማሳየቱ ይነገራል።
በፈረንጆቹ 2015 በፓሪስ በተደረገው ታሪካዊ ጉባኤ የተሳተፉት ሱልጣን ቢን አህመድ፥በኢኮኖሚክስና ማኔጀመንት ያካበቱት የላቀ እውቀት አላቸው።
በታዳሽ ሀይል ልማት ረገድም ሀገራቸውን ኤምሬትስ በልዩ ትኩረት እንድትሰራ በማድረግ ተሞክሮ የሚሆን ተግባርን ፈፅመዋል።
አቡ ዳቢ በፈረኝጆቹ 2006 "ማስዳር" የተሰኘ ታዳሽ ሀይል ልማት ያተኮረ ተቋም ስታቋቁም ሙሉ ሀላፊነቱን የሰጠችው ለሱልጣን ቢን አህመድ ነው።
"ማስዳር" የዩ ኤ ኢን የታዳሽ ሃይል ምንጭ ከማስፋትና ንፁህ የሃይል ምንጮችን ወደ ስራ ለማስገባት ጉልህ ሚና ሲጫወትም የእኝህ ባለሙያ ድርሻ በልዩነት ይነሳል።
ኤምሬትስ ከታዳሽ ሀይል በ2030 100 ጊጋዋት ለማመንጨት ለያዘችው ግብ መሳካት እየተጉ የሚገኙት ሱልጣን ቢን አህመድ፥
ከ40 በላይ ሀገራት (አብዛኞቹ የአፍሪካ ሀገራት ናቸው) የታዳሽ ሀይል ልማት ፕሮጀክቶችን በማማከርና በመሳተፍም ትልቅ አበርክቶ አላቸው።