ዶክተር ሱልጣን አልጃቢር የኮፕ28 ጉባኤ ትክክለኛው መሪ መሆናቸው ተገለጸ
አረብ ኤምሬትስ ዶ/ር ሱልጣን ቢን አህመድ አል ጃቤርን የ2023 የኮፕ28 ፕሬዝዳንት አድርጋ ሾማለች
የተባበሩት አረብ ኢምሬት የ2023 የተመድ አየር ንብረት ጉባኤ (ኮፕ28) አስተናጋጅ ሀገር ናት
ዶክተር ሱልጣን አልጃቢር የኮፕ28 ጉባኤ ትክክለኛው መሪ መሆናቸው ተገለጸ።
የተባበሩት አረብ ኢምሬት የዘንድሮውን ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ አስተናጋጅ ሀገር መሆኗ ይታወሳል።
ይህ ጉባኤ በያዝነው ዓመት መገባደጃ የመጨረሻ ወራት ላይ እንደሚካሄድ ይጠበቃል።
የተባበሩት አረብ ኢምሬት የኢንዱስትሪ ሚንስትሩ ዶክተር ሱልጣን አልጃቢር የኮፕ28 አየር ንብረት ለውጥ ጉባኤን እንዲያስተባብሩ በፕሬዝዳንትነት ተመርጠዋል።
- የአውሮፓ ህብርት ኮሚሽን ከዶ/ር ሱልጣን አልጃበር ጋር በቅርበት እየሰራሁ ነው አለ
- የኮፕ 28 ፕሬዝዳንት ሆነው የተመረጡት ሱልጣን ቢን አህመድ አል ጃበር ማን ናቸው?
አረብ ኢምሬት የነዳጅ ላኪ ሀገር መሆኗን ተከትሎ ሀገሪቱ ይህን ዓለም አቀፍ ጉባኤ ማስተናገድ የለባትም፣ ዶክተር ሱልጣን አልጃቢርም ጉባኤውን ማስተባበር የለባቸውም በሚል ተቃውሞዎች እየተሰሙ ነው።
የአሜሪካ እና አውሮፓ ህግ አውጪ ምክር ቤት አባላት በቅርቡ ዶክተር ሱልጣን አልጃቢር ከከአስተባባሪነት እንዲነሱ በፊርማ ጠይቀዋል።
ይህንን ተከትሎ ብሉምበርክ በአስተያየት አምዱ በጻፈው ሀተታ ዶክተር ሱልጣን አልጃቢር የኮፕ28 አየር ንብረት ለውጥ ትክክለኛው ሰው መሆነቸውን ጽፏል።
እንደዚህ ጽሁፍ ከሆነ ዶክተር ሱልጣን አልጃቢር የአረብ ኢምሬት ነዳጅ ስራ አስፈጻሚ ቢሆኑም በታዳሽ ሀይል ዘርፍ የተሰማራ ማስዳር የተሰኘ ኩባንያም መስራች እና ስራ አስፈጻሚ ናቸው።
አረብ ኢምሬት በቀጣዩ 10 ዓመት 100 ጊጋዋት ታዳሽ ሀይል የማመንጨት እቅድ ያላት ሲሆን የዚህ ግዙፍ እቅድ አስፈጻሚው ዶክተር ሱልጣን አልጃቢር እንደሆኑ ተገልጿል።
ዶክተር ሱልጣን በዚህ ስራቸው አብዛኛው የአሜሪካ እና አውሮፓ ህግ አውጪ ምክር ቤት አባላት ድጋፍ አላቸውም ተብሏል።
ከዚህ በተጨማሪም የአሜሪካ አየር ንብረት ልኡክ ጆን ኬሪ፣ የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን መሪ ኡስሩላ ቮንደርሊን እና አብዛኛው የዓለማችን ሀገራትም ድጋፍ እንዳላቸውም በዚህ ዘገባ ላይ ተጠቅሷል።
ዓለማችን ታዳሽ ሀይል በፍጥነት እንዲስፋፋ እና ጥቅም ላይ እንዲውል ብትፈልግም ይህን ግን ባንድ ጊዜ መቀየር ስለማይቻል የነዳጅ ሀይልን መጠቀማችን ይቀጥላልም ተብሏል።