በሁለት ግንባር የተሰለፉት ድሮን አዳኝ የተባሉት የዩክሬን ዳኛ
ብላዲስላቭ የተባሉት የዩክሬን ዳኛ ሀገራቸውን በመዶሻ እና በጠብመንጃ ማገልገል እንደሚችሉ በተረዱ ጊዜ ወዲያውኑ ነበር ወደ ውጊያ የገቡት

ዳኛው እንዳሉት ጦርነቱ እያየለ በሄደበት ወቅት ሴት ልጆቻቸው ሀገር ውስጥ ለመቆየት በመወሰናቸው ምክንያት በውጊያ ለመሳተፍ እንዲወስኑ አድርጓቸዋል
ብላዲስላቭ የተባሉት የዩክሬን ዳኛ ሀገራቸውን በመዶሻ እና በጠብመንጃ ማገልገል እንደሚችሉ በተረዱ ጊዜ ወዲያውኑ ነበር ወደ ውጊያ የገቡት።
ቀን ላይ በጦርነት ወቅቱ ያለው የፍትህ ስርአት እንዲቀጥል እና ህግ እንዲከበር ከዩክሬን ዋና ከተማ ኪቭ ውጭ ይሰራሉ።
ብላዲስላቭ ሌሊት ደግሞ በአብዛኛው ከሌሎች ዳኞች፣ ከህግ አስከባሪ አካላት እና ከሌሎች ስራተኞች የተውጣጣውን በጎፈቃደኛ ቡድን በመቀላቀል መብረት ወደ ሰማይ በማብራት የሩሲያ ድሮኖችን በመለየት መትተው ይጥላሉ።
ዳኞች ለወታደርነት እንዲመለመሉ አይገደዱም። ነገርግን ዳኛው እንዳሉት ጦርነቱ እያየለ በሄደበት ወቅት ሴት ልጆቻቸው ሀገር ውስጥ ለመቆየት በመወሰናቸው ምክንያት በውጊያ ለመሳተፍ እንዲወስኑ አድርጓቸዋል።
"እንደ አባት እነሱን ከጥቃት ልጠብቃቸው ይገባል" ይላሉ ዳኛው።"ቤተሰቦቼ ዩክሬንን መርጠዋል።"
በጦር ግንባር እየገሰገሱ ያሉት የሩሲያ ኃይሎች በዩክሬን ከተሞች ላይ የሚያደርጉትን ድብደባ ጨምረዋል፤ ዋና ትኩረታቸው ደግሞ የኃይል መሰረተልማቶች ናቸው። የሩሲያ ኃይሎች ዋና ትኩረታቸውን የኃይል መሰረተልማት ላይ ያደረጉት የዩክሬናውያን ከፍተኛ የኃይል አቅርቦት የሚፈልጉበት ክረምት እየገባ በመሆኑ እንዲቸገሩ ለማድረግ እንደሆነ ይገለጻል።
ጥቃት ለመሰንዘር የሚመጡ የሩሲያ ድሮኖችን የመለየት ስራ ብዙ ጊዜ የሚሰጠው በዘፈቀደ ለተመረጡ ሰዎች እና በጎ ፈቃደኞች ነው።
የቱስኩሮቭ ዩኒት ወይም ድሪም የተባለው የበጎፈቃደኞች ቡድን አብዛኛው አባላቱ ዳኞች ሲሆኑ የተቋቋመው ሩሲያ በዩክሬን ልዩ ያለችውን ወታደራዊ ዘመቻ በየካቲት 2022 ከጀመረች በኋላ ነበር።
በጎፈቃደኞቹ የሚያሳልፏቸው እንቅልፍ አልባ ሌሊቶች በቀን በሚከውኗቸው ስራዎች ላይ ተጨማሪ ጫና እያሳደሩባቸው ነው።
ሶስት አመት ሊሞላው ጥቂት ወራት ብቻ የሚቀሩት የሩሲያ- ዩክሬን ጦርነት በቅርቡ ምዕራባውያን ዩክሬን የረጅም ርቀት ተጠቅማ ሩሲያን እንድታጠቃ መፍቃዳቸው እና ሩሲያ ይህን ተከትሎ ኦሬሽኒክ የተባለ አዲስ ሚሳይል መተኮሷ በከፍተኛ ሁኔታ ተባብሶ ተስተውሎ ነበር።