በኤጂያን ባህር የተነሳ የመሬት መንቀጥቀጥ ቱርክና ግሪክን አንቀጠቀጠ
በፈረንጆቹ 1999 በተከሰተ የመሬት መንቀጥቀጥ በእዝመር ከ17ሺ በላይ ሰዎች መሞታቸው ይታወሳል
7.0 መጠን ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ በቱርኳ የወደብ ከተማ ስድስት ህንጻዎች እንዲደረመሱ አድርጓል
7.0 መጠን ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ በቱርኳ የወደብ ከተማ ስድስት ህንጻዎች እንዲደረመሱ አድርጓል
በኤጂያን ባህር የተከሰተ ጠንካራ የመሬት መንቀጥቀጥ ቱርክና ግሪክ ደርሶ ህንጻዎች እንዲደረመሱ ምክንያት ሆኗል፤ የመንግስት ሚኒስትር ደግሞ ሰዎች በአደጋው መጠላፋቸውን ገልጸዋል፡፡
በቱርኳ ወደብ አቅራቢያ በምትገኘው እዝመር ከተማ ያሉ እማኖች ለሮተርስ እንደገለጹት 7.0 በሬክር ስኬል ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ ከተከሰተ በኋላ ሰዎች ወደ ጎዳና ወጥተው ነበር፡፡ የመሬት መንቀጥቀጡ እስከ ቱርኳ ኢስታንቡልና ግሪክ ደሴቶች መድረሱን የተገለጸ ሲሆን ባለስልጣናት ምንም ጉዳት ባይከሰትም ብዙ ሰው ጭንቅ ውስጥ ነው ብለዋል፡፡
የቱርክ የሀገር ውስጥ ሚኒስትር ሱሌማን ሶይሉ በእዝመር ከተማ በምትገኘው ስድስት ህንጻዎች መደርመሳቸውን ተናግረዋል፡፡ የአርበናይዜሽን ሚኒስትር ሙራት ኩሩም የተደረመሱት ህንጻዎች ስድስት መሆናቸውንና በፍርስራሾቹ ውስጥ ሰዎች መኖራቸውን ገልጸዋል፡፡ የእዝመር ከንቲባ እንዳሉት ደግሞ 20 ህንጻዎች በመሬት መንቀጥቀጥ ተደርምሰዋል፡፡
ሶልዩ እንደገለጹት የመሬት መንቀጥቀጡ በተሰማባቸው ስድስት ግዛቶች ጉዳት አልደረሰም ብለዋል፡፡ ቱርክ ለመሬት መንቀጥቅ ተጋላጭ ከሆኑ ሀገራት መካከል አንዷ ነች፡፡
በፈረንጆቹ 1999 በተከሰተ 7.6 መጠን ባለው የመሬት መንቀጥቀጥ በእዝመር ከ17ሺ በላይ ሰዎች መሞታቸው ይታወሳል፡፡ በፈረንጆቹ 2011 በተፈጠረ የመሬት መንቀጥቀጥ በምስራቃዊቷ ቫን 500 ሰዎች ሞተዋል፡፡