ከእሁድ ጀምሮ በተቀሰቀሰው ጦርነት በርካታ ሰዎች ሲገደሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ቆስለዋል
ከእሁድ ጀምሮ በተቀሰቀሰው ጦርነት በርካታ ሰዎች ሲገደሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ቆስለዋል
የአርመኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኒኮል ፓሺኒያን ቱርክ በድጋሚያ የዘርማጥፋት መንገድ ላይ ትገኛለች፤የአንካራ ጦር የአዘርባጃን ወታሮችን በመምራት በአርመኖች ላይ ቀጥተኛ ጥቃት እየፈጸመ ነው በማለት በቱርክ ላይ ክስ አቅርበዋል፡፡
የነዳጅ ዘይትና ጋዝ መስመር በተዘረጋበት ቀጣና ላይ ከባፈው እሁድ ጀምሮ በተቀሰቀሰው ጦርነት በርካታ ሰዎች መገደላቸውንና በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መቁሰላቸው ተዘግቧል፡፡
ክስተቱ በቀጣናው ከፍተኛ አለመረጋጋት ያመጣል ተብሎ ተሰግቷል፡፡
የፈረንሳይ፣ የሩሲያና የአሜሪካ ፕሬዘዳንቶች በአዘርባጃንና በአርመኒያ መካከል ያለው ጦርነት እንዲቆም ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን ነገርግን ቱርክና አዘርባጃን ሶስቱ ኃያላን በሰላም እንቅስቃሴው ዙሪያ ምንም ሚና ሊኖራቸው አይገባም ብለዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ፓሽኒያን እንዳሉት ሁኔታው ከዚህ በፊት ከነበሩት ጥቃቶች አስከፊ ነው፤ ይህን በፈረንጆቹ 1915 ከተፈጸመውና 1.5 ሚሊዮን አርመኖች ከተገደሉበት ጭፍጨፋ ጋር ማነጻጸሩ ተገቢ ይሆናል ብለዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የባለፈውን የካደችው ቱርክ በድጋሚ የዘር ማጥፍት እንቅስቃሴ ውስጥ መግባቷን ገልጸዋል፡፡
ቱርክ በድሮው ኦቶማን ግዛት በርካት አርመኖች በአንደኛው የአለም ጦርነት በተፈጠረ ግጭት መገደላቸውን ብትገልጽም፤ ቱርክ ግድያው የተቀነባበረና የዘርማጥፋት መሆኑን አትቀበልም፡፡