በምስራቅ አፍሪካ በየ48 ሰከንዱ አንድ ሰው በኑሮ ውድነትና ግጭት ምክንያቶች እየሞተ ነው ተባለ
ዩኒሴፍና ኦክስፋም በጋራ ባወጡት ሪፖርት በምስራቅ አፍሪካ 181 ሚሊየን ሰዎች በግጭቶች ምክንያት ተጎድቷል
ሰዎች እየሞቱ ያሉት በኢትዮጵያ፣ ኬንያ እና ሶማሊያ ነው ተብሏል
በምስራቅ አፍሪካ በየ48 ሰከንዱ አንድ ሰው በኑሮ ውድነት እና ግጭት ምክንያቶች እየሞተ ነው ተባለ።
በምስራቅ አፍሪካ ባሉ ግጭቶች፣ የኑሮ ውድነት እና ረሀብ ምክንያቶች በእያንዳንዷ 48 ሰከንድ ውስጥ አንድ ሰው እየሞተ መሆኑን መቀመጫውን ለንደን ያደረገ ኦክስፋም የተሰኘው መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ባወጣው ሪፖርት ገልጿል፡፡
ድርጅቱ እንዳለው በምስራቅ አፍሪካ ባለፉት ሁለት ዓመታ ውስጥ በነበሩ የዝናብ ወቅቶች ዝናብ ባለመዝነቡ ምክንያት በ40 ዓመት ውስጥ አስከፊ የሚባል ድርቅ ተከስቷል።
ድርቁ በተለይም በሶማሊያ፣ ኢትዮጵያ እና ኬንያ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰ ሲሆን ከሶስት ሚሊዮን በላይ እንስሳት በዚሁ ድርቅ ምከልንያት ሞተዋል።
ይህ መሆኑ ደግሞ የምግብ ዋስትናቸው አደጋ ውስጥ መውደቁን የጠቀሰው ይህ ድርጅት አካባው ከዚህ በፊት በአንበጣ መንጋ እና በግጭት የተጎዳ መሆኑ አደጋውን የከፋ አድርጎታል።
አሁን ደግሞ ድርቁ ያስከተለው ጉዳት እንዳለ ሆኖ በሶስቱ ሀገራት ባሉ ግጭቶች እና የኑሮ ውድነት ባስከተለው የምግብ ዋጋ መጨመር ምክንያት በእያንዳንዷ 48 ሰከንድ ውስጥ አንድ ሰው እየሞተ መሆኑን አስታውቋል።
የዓለም ህጻናት አድን ድርጅት እና ኦክስፋም በጋራ ባወጡት ሪፖርት መሰረት በምስራቅ አፍሪካ 181 ሚሊዮን ህዝብ በግጭቶች የተጎዳ ሲሆን ህጻናት እና ሴቶች ደግሞ ዋነኛ የጉዳት ሰለባ እንደሆኑም ገልጸዋል።
እንደ ሁለቱ ድርጅቶች ሪፖርት ከሆነ በምስራቅ አፍሪካ ያጋጠመው የረሃብ አደጋ የፖለቲካ ውድቀት ሲሆን፤ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የተለያዩ ጥረቶችን እንዳላደረጉ ጠቅሶ አሁንም ቀጣይ ግጭቶችን እንዲያስቆሙ ጠይቀዋል።