በርካታ የዓለማችን ሀገራት የፋሲካ በዓልን እያከበሩ ናቸው
የክርስትና ዕምነት ተከታዮች በዛሬው ዕለት የፋሲካ በዓልን እያከበሩ ይገኛሉ
በዓሉ የኢየሱስ ክርስቶስ ሞትን ድል አድርጎ መነሳቱን ተከትሎ የትንሳኤ በዓል በሚል በየዓመቱ ይከበራል
በርካታ የዓለማችን ሀገራት የፋሲካ በዓልን እያከበሩ ናቸው፡፡
በክርስትና ዕምነት ተከታዮች ዘንድ ከሚከበሩ በዓላት መካከል አንዱ የሆነው የትንሳኤ ወይም የፋሲካ በዓል በተለያዩ ሀገራት እየተከበረ ይገኛል፡፡
የፋሲካ በዓል ኢየሱስ ክርስቶስ የሰው ልጆችን ለማዳን እና ለማስተማር ወደ ምድር በመጣበት ጊዜ በደረሰበት እንግልት ህይወቱ ካለፈ እና በተቀበረ በሶስተኛው ቀንም ሞትን ድል አድርጎ መነሳቱን ተከትሎ የሚከበር በዓልም ነው፡፡
ባሳለፍነው አርብ ዕለት የስቅለት በዓልን ያከበሩ የክርስትና ዕምነት ተከታዮች ዛሬ ደግሞ የትንሳኤ በዓልን አክብረዋል፡፡
በዓሉ በተለያዩ ሀገራት በተለያዩ ጊዜ እና ባህል መሰረት የሚከበር ሲሆን ሀገራት የሚከተሉት የዘመን አቆጣጠር በዓሉ በመላው ዓለም በአንድ ቀን እንዳይከበር ዋነኛ ምክንያት እንደሆነ ይገለጻል፡፡
ቢቢሲ እንደዘገበው በዓሉ በድምቀት በተከበረባቸው ሀገራት ያሉ አከባበሮችን በምስል አጋርቷል፡፡