ፋሲካን ከኢትዮጵያ ጋር የሚያከብሩ ሀገራት የትኞቹ ናቸው?
ኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ግብጽ፣ ሩስያና ዩክሬንን ጨምሮ በርካ ሀገራት የፋሲካ በዓልን በዛሬው እለት እያከበሩ ነው
የጎርጎሮሳውያኑን የዘመን ቀመር የሚከተሉ ሀገራት ክርስቲያኖች ፋሲካን ከሳምንት በፊት ማክበራቸው ይታወሳል
የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳዔ (ፋሲካ) በምስራቅ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አማኞች (ኦሪዬንታል ኦርቶዶክስ) ዘንድ በዛሬው እለት እየተከበረ ነው።
ኢትዮጵያን ጨምሮ የጁሊያን የዘመን ቀመር የሚከተሉት ሀገራት ናቸው በተለያዩ ሃይማኖታዊ እና ባህላዊስነስርአቶች በዓሉን እያከበሩ የሚገኙት።
ከአለማችን ህዝብ 12 ከመቶው የኦርቶዶክስ ክርስቲያን መሆኑን ታይም መጽሄት ይዞት በወጣው መረጃ ያመላክታል።
እስከ 300 ሚሊየን የሚደርሱ ሰዎች የኦርቶዶክስ ክርስትና እምነትን እንደሚከተሉም ነው ግምቱን ያስቀመጠው።
በምስራቅ አውሮፓ፣ መከከለኛው ምስራቅና በአፍሪካ ኢትዮጵያ እና ግብጽ ከፍተኛ የእምነቱ ተከታዮች ቁጥር ይገኝባቸዋል።
የዘመን ቀመሯን ከኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ጋር ያዋደደችው ኢትዮጵያ የ2015 የትንሳዔ (ፋሲካ) በዓልን በዛሬው እለት እያከበረች ትገኛለች።
ከ15 ሚሊየን በላይ የግብጽ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ አማኞችም የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳዔ (ፋሲካ) በዓልን በዛሬው እለት እያከበሩት ነው።
የሩሲያ ኦርቶድክስ እምንት ተከታዮችም የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳዔ (ፋሲካ) በዓልን በዛሬው እለት በማከበር ላይ መሆናቸውም ታውቋ።
የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያናት በሚገኙባቸው ኤርትራ፣ እስራኤል፣ አርመኒያ፣ ሰርቢያ፣ ቤላሩስ፣ ሞንቴኔግሮ፣ ቡልጋሪያ፣ መቄዶኒያ፣ ጆርጂያ እና ሞልዶቫም የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳዔ (ፋሲካ) በዓል በዛሬው እለት እየተከበረ ነው።