የዘንድሮው ፋሲካ በዓል ገበያ ቅኝት በአዲስ አበባ
የዘንድሮው በዓል ገበያ በኑሮ ውድነት እና ሌሎች ምክንያቶች መቀዝቀዙን ሸማቾች እና ነጋዴዎች ተናግረዋል
የዶሮ ዋጋ ከአምናው ጋር ሲነጻጸር እስከ 500 ብር ድረስ ጭማሪ አሳይቷል ተብሏል
የትንሳኤ አልያም የፋሲካ በዓል በክርስትና ዕምነት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት ከሚከበሩ በዓላት መካከል አንዱ ነው።
ሁሌ እሁድ ዕለት የሚከበረው ይህ በዓል ለበዓሉ ማድመቂያ የሚሆኑ ግብይቶች ምን እንደሚመስሉ ዓልዐይን አማርኛ በአዲስ አበባ ተዘዋውሮ ተመልክቷል።
- ለፋሲካ በዓል የተገዛው አውራ ዶሮ ጎረቤቶችን አላስተኛ ብሏል በሚል ክስ ተመስርቶበታል
- የፋሲካ በዓልን በማስመልከት በዩክሬን የተኩስ አቁም እንዲደረግ ተመድ ጠየቀ
ለፋሲካ በዓል የተገዛው አውራ ዶሮ ጎረቤቶችን አላስተኛ ብሏል በሚል ክስ ተመስርቶበታል
ሸጎሌ፣ ሾላ እና ካራ የገበያ ስፍራዎች ደግሞ የገበያውን ቅኝት ያደረግንባቸው አካባቢዎች ሲሆኑ የበሬ፣በግ፣ፍየል፣አትክልት እና ሌሎች ለበዓሉ ማድመቂያ የሚሆኑ ምርቶች ናቸው።
በሸጎሌ ፣ካራ እና አካባቢው ባለው ገበያ በሬ ከ40 ሺህ ጀምሮ እስከ 150 ሺህ ብር ድረስ እየተሸጠ ይገኛል።
በአብዛኛው ግን መካከለኛ በሬ በተለይም ለቅርጫ የሚሆን በሬ ከ60 ሺህ እስከ 90 ሺህ ብር ድረስ በብዛት ሲሸጥ ታዝበናል።
በግ ደግሞ አነስተኛው ከ5 ሺህ ጀምሮ እስከ 20 ሺህ ብር ድረስ በመሸጥ ላይ ሲሆን መካከለኛ በግ እስከ 10 ሺህ ብር እየተሸጠ መሆኑን አይተናል።
በዘንድሮው የፋሲካ በዓል ላይ ምልከታ ባደረግንባቸው ገበያዎች ላይ ፍየል በብዛት አለመቅረቡን የታዘብን ሲሆን ከ10 ሺህ ጀምሮ እስከ 28 ሺህ ድረስ እየተሸጠ ይገኛል።
ዶሮ ደግሞ ከ600 ብር እስከ 1ሺህ 800 ድረስ በመሸጥ ላይ ሲሆን እንቁላል ከ10 ብር እስከ 12 ብር ድረስ እየተሸጠ ነው።
ከስጋ ውጪ ያሉ የበዓሉ ማድመቂያ ግብይቶችን የታዘብን ሲሆን ዘይት ባለ አምስት ሊትር ከ900 ብር እስከ 1800 ብር ድረስ በመሸጥ ላይ ነው።
የአትክልት ምርቶችም የዋጋ ጭማሪ የታየባቸው ሲሆን ሽንኩርት በኪሎ ከ38-50 ብር ድረስ ባለው ዋጋ በመሸጥ ላይ ነው።
ቡላ በኪሎ ከ160 እስከ 170 ብር እንዲሁም ቆጮ 110 እስከ 120 ብር በኪሎ በመሸጥ ላይ መሆኑንም ታዝበናል።
ቂቤ ደግሞ ለጋው አንድ ኪሎ ከ840 እስከ 850 እንዲሁም መካከለኛ የሚባለው ቅቤ ከ730 እስከ 750 ብር እየተሸጠ መሆኑን አይተናል።
ሌላኛው የበዓል ማድመቂያ ሽንኩርት ሲሆን ቀይ የሀበሻ ሽንኩርት አንድ ኪሎ 100 ብር፣ እንዲሁም ፋሮ አልያም
የፈረንጅ ቀይ ሽንኩርት ደግሞ በሾላ ገበያ በ50 ብር እየተሸጠ ይገኛል።
እንዲሁም ነጭ ሽንኩርት ደግሞ ከ200 እስከ 240 ብር ድረስ እየተሸጠ ሲሆን ዝንክብል በኪሎ እስከ 80 ብር እየተሸጠ ይገኛል።
እንዲሁም ቲማቲም ደግሞ አንድ ኪሎ ከ30 እስከ 35 ብር ድረስ እየተሸጠ ነው።
የዘንድሮው ፋሲካ በዓል ከዓምናው ጋር ጋር ሲነጻጸር የዶሮ ዋጋ እስከ 500 ብር ድረስ በግ ደግሞ ከሁለት ሺህ እስከ አራት ሺህ ድረስ ጭማሬ ማሳየቱን ያነጋገርናቸው ሸማቾች እና ነጋዴዎች ነግረውናል።