ግብጽ በሀጅ ወቅት የጠፉ የዜጎቿን ለማግኘት ግብረ ኃይል አቋቋመች
ካይሮ በሳዑዲ አረቢያ ሀጅ ሲያደርጉ የጠፉ ዜጎቿን ልታፈላልግ ነው
በዘንድሮው የሀጂ ጉዞ የ30 ሰዎች ህይወት አለፈ
የግብጽ ኢሚግሬሽን ሚንስቴር እና የስደተኞች ጉዳይ በሳዑዲ አረቢያ ሀጅ ሲያደርጉ የጠፉ የቤተሰብ አባላትን ለማግኘት የሚረዳ ግብረ ኃይል ማቋቋሙን አስታውቀዋል።
የኢሚግሬሽን ሚንስትር ሶሃ ጄንዲ ግብረ ኃይሉ የተቋቋመው በመካ ሳዑዲ አረቢያ በሀጅ ስነ-ስርዓት ላይ ቤተሰቦቻቸው የጠፉባቸው ሰዎች ያቀረቡትን አቤቱታ ተከትሎ ነው።
ግብረ ኃይሉ በሳዑዲ አረቢያ ከሚገኘው የግብጽ ኤምባሲና ከሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር ጥረቱን እንደሚያስተባብር መግለጫው ተመልክቷል።
ሚንስትሯ እንዳረጋገጡት የጠፉ ሰዎች ህይወታቸው አለፎ ከሆነ ቤተሰቡ በሳዑዲ አረቢያም ሆነ በግብጽ የመቅበር አማራጭ ይኖረዋል።
ከአምስት እስከ ስድስት ቀናት በላይ የሚፈጀው ሀጅ ዘንድሮ ከሰኔ 26 እስከ ሀምሌ አንድ ተካሂዷል። በኃይማኖታዊ ስነ-ስርዓቱ ላይ ሁለት ሽህ የሚደርሱ ሰዎች በከፍተኛ የሙቀት ማዕበል መታመማቸው ተነግሯል።
እስከ አርብ ድረስ የ30 ሰዎች ህይወት አልፏል የተባለ ሲሆን፤ የሞቱ ምክንያት ግን እስካሁን አልተገለጸም።
አህራም ኦንላይን እንደዘገበው ጄንዲ በሀጅ ወቅት ቤተሰቦቻቸውን ላጡ ወገኖች ሀዘናቸውን ገልጸው፤ የስደተኞች ጉዳይ ሚንስቴር ተገቢውን ድጋፍ ለማድረግ ቁርጠኛ እንደሆነ አረጋግጠዋል።