ዋሸንግተን ከዚህ በፊት ሚሳኤሎቹን የሸጠችው ወዳጅ ለምትላቸው ሀገራት ብቻ ነው
ግብጽ ከአሜሪካ በገፍ ለመግዛት የተስማማችው ስቲንጀር ሚሳኤል ምንድን ነው?
የዓለማችን ልዕለ ሀያል የሆነችው አሜሪካ ለግብጽ ስቲንጀር የተሰኘውን ሚሳኤል ለመሸጥ ተስማምታለች፡፡
ግብጽ 720 ስቲንጀር ሚሳኤሎችን ለመግዛት ከአሜሪካ ጋር የተስማማች ሲሆን መሳሪያዎቹ በቀላሉ የሚተኮሱ፣ ዋጋቸው ርካሽ እና አንድ ወታደር በትከሻው ላይ አድርጎ በቀላሉ አውሮፕላኖችን እና ሎጅስቲክ ማዕከላትን መምታት የሚያስችሉ ናቸው፡፡
በቅርብ ርቀት ውስጥ የሚደረጉ ውጊያዎችን የበላይነት ለመያዝ ይጠቅማሉ የሚባሉት ስቲንጀር ሚሳኤል የአንዱ ዋጋ 38 ሺህ ዶላር ነው፡፡
ግብጽ ሁለተኛ ዙር ከፍተኛ መጠን ያለው የጦር መሳርያ ለሶማሊያ ድጋፍ ማድረጓ ተነገረ
ግብጽ ይህን ሚሳኤል ከመግዛት ባለፈ የቁሳቁስ፣ ትገና እና ሌሎች ድጋፎችንም ከአሜሪካ እንደምታገኝ ተገልጿል፡፡
አሜሪካ መሰል ወታደራዊ ምርቶችን ብሔራዊ ጥቅሞቼን ያስጠብቃሉ ለምትላቸው እና ወዳጅ ለምትላቸው ሀገራት ብቻ የምትሸጥ ሲሆን ለግብጽ የተደረገው የግዢ ስምምነትም የዚሁ አካል ነው ተብሏል፡፡
የአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት የሽያጭ ስምምነቱን አስመልክቶ እንዳለው ግብጽ ሉዓላዊነቷን ለማስከበር፣ ህዝቦቿን ለመጠበቅ እና መሰረተ ልማቶቿን እንድትጠብቅበት የስቲንጀር ሚሳኤል ግዢ ስምምነት መደረጉን ገልጿል፡፡
አንዱ የስቲንጀር ሚሳኤል 10 ኪሎ ግራም ክብደት ያለው ሲሆን በሰዓት 2 ሺህ 400 ኪሎ ሜትር የመጓዝ አቅም አለውም ተብሏል፡፡
ሚሳኤሉ ከተሽከርካሪ ላይ እና ከሰው ትከሻ ላይ መተኮስ የሚችል ሲሆንበ8 ኪሎ ሜትር ርቀት ውስጥ ያለ ኢላማን መምታት እንደሚልም ተገልጿል፡፡
እንዲሁም ይህ ሚሳኤል ከወታደር በተጨማሪ ስልጠናውን በወሰደ ሲቪል ሰውም ሊተኮስ ይችላል የተባለ ሲሆን በተለይም የምድር ለይ ውጊያዎችን የበላይነት ለመውሰድ ተመራጭ ነው፡፡