በመቶዎች የሚቆጠሩ የሀጅ ተጓዥ ዜጎቿ የሞቱባት ግብጽ ጉዳዩን ለመመርመር ኮሚቴ አቋቋመች
የግብጽ ካባኔ በመደበኛ ሁኔታ ተመዝግበው በሀጅ ከተሳተፉት 50,752 ሰዎች ውስጥ የሞቱት 28 ብቻ መሆናቸውን ገልጿል
ባለፉት ቀናት በሳኡዲ አረቢያ ለሀጅ የተገኙ የተለያዩ ሀገራት ዜጎች እስከ 51 ዲግሪ ሴልሸስ በደረሰው ከባድ ሙቀት ሳቢያ ህይወታቸው ማለፉ ተዘግቧል
ግጽ በዘንድሮው የሀጅ ጉዞ የተሳተፉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ዜጎቿ በመካ በነበረው ከባድ ሙቀት ወቅት መሞታቸውን ተከትሎ ጉዳዩን የሚመረምር የቀውስ ጊዜ ኮሚቴ ማቋቋን ባለፈው ሀሙስ እለት አስታውቃለች።
ግብጽ ይህን ኮሚቴ ያቋቋመችው የህክምናና የደህነት ምንጮች በሀጅ ጉዞ ከተሳፉ ግብጻውያን መካከል 530 መሞታቸውን እና 31 የሚሆኑት ደግሞ መጥፋታቸውን ከገለጹ በኋላ ነው።
ባለፉት ቀናት በሳኡዲ አረቢያ ለሀጅ የተገኙ የተለያዩ ሀገራት ዜጎች እስከ 51 ዲግሪ ሴልሸስ በደረሰው ከባድ ሙቀት ሳቢያ ህይወታቸው ማለፉ ተዘግቧል።
ከግብጽ የሀጅ ሉካን ቡድን ጋር የነበረ የህክምና ምንጭ እንደገለጸው ከሆነ ከሞቱት ውስጥ አብዛኞቹ ለመሳፍ በመደበኛ ሁኔታ ያልተመዘገቡ ናቸው፤ ይህ ማለት መጠለያ ድንኳን አልነበራቸውም ማለት ነው።
በፕሬዝደንት አል ሲሲ ትዕዛዝ መሰረት የኮሚቴውን መቋቋም ይፋ ያደረገው የግብጽ ካባኔ በመደበኛ ሁኔታ ተመዝግበው በሀጅ ከተሳተፉት 50,752 ሰዎች ውስጥ የሞቱት 28 ብቻ መሆናቸውን ገልጿል።
ካልተመዘገቡት ውስጥ የሞቱት ምን ያህል እንደሆኑ ያልጠቀሰው ካቢኔው፣ ግብጽ በትክክል ምን ያህል ዜጎቿ እንደሞቱ እና እንደጠፉ ለማወቅ ትፈልጋለች፤ የሟቾችን አስከሬንም ወደ ሀገራቸው ለማምጣት ከሳኡዲ አረቢያ ባለስልጣናት ጋር እየተባበረች ነው ብሏል።
ካቢኔው አክሎም እንደገለጸው ላልተመዘገቡ የሀጅ ተጓዦች ጉዞ ያመቻቹ ኩባንያዎች ምርመራ ተደርጎ ይቀጣሉ።
በሀጅ ስነ ስርአቱ ወቅት በሺዎች የሚቆጠሩ ምዕመናን መንገድ ላይ እና ወደ አረፋት ተራራ በሚወጡበት ወቅት ለጸሀይ ተዳርገው እንደነበር ሮይተርስ የአይን እማኞችን ጠቅሶ ዘግቧል።
የህክምና መኪና በቦታው እስከሚደርስ ድረስ የሞቱ ሰዎች አስከሬን በኢህራም ልብስ ወይም በተጓዦቹ በሚለበስ ቀላል ጨርቅ ተሽፍኖ ነበር።
ሀጅ በእስልምና እምነት ውስጥ አንደኛው ምሰሶ ሲሆን ማንኛውም የሚችል ሙስሊም በህይወቱ አንድ ጊዜ ሀጅ እንዲከውን ይጠበቅበታል። ከሳምንት በፊት የተጀመረው ስነስርአት ከሁለት ሚሊዮን ሰዎች በላይ ሊታደሙ እንደሚችሉ ተገልጾ ነበር።
በሀጅ ወቅት ከሙቀት ጋር የተያያዘ ሞት ከ1400ዎቹ ጀምሮ የተመዘገበ ቢሆንም እያደገ የመጣው የሙቀት መጠን በስነስርዓቱ ላይ ስጋት ሊፈጥር እንደሚችል ሳይንቲስቶች እየተናሩ ናቸው።