ፖለቲካ
ግብጽ በታህሳስ ወር በምታደርገው ምርጫ ፕሬዝዳንት አልሲሲ እንደሚያሸንፉ ይጠበቃል
ካይሮ ባደረገችው የህገ-መንግስት ማሻሻያ ፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ አልሲሲ ለሦስተኛ ዘመን መወዳደር ይችላሉ
አልሲሲ የ2014ቱንና የ2018ቱን ምርጫ 97 በመቶው ድምጽ በማግኘት ማሸነፋቸው የሚታወስ ነው
ግብጽ ከፈረንጆቹ ታህሳስ 10 እስከ 12 ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ታካሂዳለች።
- “የግብጽ ጦር ጠንካራ አቅም ካላቸው ሃያል የመካከለኛው ምስራቅ ጦሮች መካከል አንዱ ነው”-አል ሲሲ
- በህዳሴው ግድብ ጉዳይ ግብጻውያን ሊታገሱ እንደሚገባ ፕሬዝዳንት አል ሲሲ ተናገሩ
ምንም እንኳ ሀገሪቱ ከፍተኛ የዋጋ ግሽበትና የውጭ ምንዛሬ እጥረትን የመሰሉ የምጣኔ-ሀብት ቀውሶች እየተፈተነች ቢሆንም ፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ አል ሲሲ ዳግም ይመረጣሉ ተብሎ በሰፊው ይጠበቃል።
68 ዓመታቸውን የያዙት ሲሲ በ2019 በተደረገ የህገ-መንግስት ማሻሻያ ለሦስተኛ ዘመን መወዳደር ይችላሉ።
የህገ-መንግስት ማሻሻያው አራት ዓመት የነበረውን የአንድ የስልጣን ዘመን ወደ ስድስት ዓመት ከፍ ያደረገ ሲሆን፤ ይህም ፕሬዝዳንት አል ሲሲ እስከ 2030 ድረስ መንበሩ ላይ እንዲቆዩ በር ከፍቷል።
ምንም እንኳ ሲሲ በይፋ እጩነታቸውን እስካሁን ቢያስታውቁም፤ መንግስትታዊ ፓርቲዎች ቢልቦርዶችን በመለጠፍ የምርጫ ዘመቻውን ጀምረዋል።
ፕሬዝዳንት ሲሲ የ2014ቱንና የ2018ቱን ምርጫ 97 በመቶው ድምጽ በማግኘት አሸንፈዋል።
ፕሬዝዳንቱ በ2018ቱ ምርጫ ዋና ተፎካካሪያቸው ከታሰሩና ሌሎቹ በጫና ምክንያት ከውድድሩ ራሳቸውን ካገለሉ በኋላ በአንድ ተቀናቃኝ ብቻ ምርጫውን ማሸኘፋቸው ይታወሳል።
የካይሮ የምርጫ ባለስልጣን እንዳስታወቀው የምርጫ ውጤት በአራተኛ ቀኑ ይገለጻል።