አልበርት አንስታይን ኑክሌር ቦምብ እንዲሰራ የፈረመበት ደብዳቤ በ6 ሚሊዮን ዶላር ጨረታ ቀረበ
ደብዳቤው አንስታይን አሜሪካ በፍጥነት የኑክሌር ቦምብ እንድትሰራ የሚጠይቅ ነበር
አንስታይን ጅምላ ጨራሽ ቦምቡ ከተሰራ በኋላ ተጸጽቻለሁ ማለቱ ይታወሳል
አልበርት አንስታይን ኑክሌር ቦምብ እንዲሰራ የፈረመበት ደብዳቤ በ6 ሚሊዮን ዶላር ጨረታ ቀረበ፡፡
የዓለማችን ዝነኛ ሳይንቲስት እንደሆነ የሚነገርለት አልበርት አንስታይን ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ከመቀስቀሱ በፊት በወቅቱ ለነበሩት የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ፍራንክሊን ሩዝቬልት አንድ ከባድ መልዕክት እና ሚስጥር የያዘ ደብዳቤ ጽፎ ነበር፡፡
ይህ ደብዳቤ ከእነ አሜሪካ ጎራ በተቃራኒ ያለችው የአዶልፍ ሂትለሯ ጀርመን የኑክሌር ቦምብ ልትሰራ እንደምትችል የሚያስጠነቅቅ ሲሆን በደብዳቤው ላይ የአንስታይን ፊርማ አርፎበታል፡፡
ፕሬዝዳንት ሩዝቬልት የሳይንቲስቶቹን አስተያየት ከግምት ውስጥ በማስገባት በፈረንጆቹ 1939 ላይ የማንሀተን ፕሮጀክት በሚል የኑክሌር ቦምብ ማምረት ስራ አስጀምረዋል፡፡
በአንስታይን ምክረ ሀሳብ መሰራት የጀመረው ይህ ቦምብም ለመጀመሪያ ጊዜ በ1945 በጃፓን ሂሮሽማ እና ናጋሳኪ ላይ መሞከሩ አይዘነጋም፡፡
የኑክሌር ጦርነት ቢቀሰቀስ ዓለም ምን ያጋጥማታል?
ይህ ታሪካዊ ደብዳቤ ከዚህ በፊት በወጣ ጨረታ የማይክሮ ሶፍት ኩባያ አንዱ መስራች የሆኑት ፖል አለን ተገዝቶ ንብረትነቱም የዚህ ግለሰብ ሆኗል፡፡
በድጋሚ የፊታችን መስከረም ወር ላይ ለጨረታ ይቀርባል የተባለ ሲሆን መነሻ ዋጋውም ስድስት ሚሊዮን ዶላር ዋጋ እንደወጣለት ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
እንደ ዘገባው ከሆነ የፊታችን መስከረም በኒዮርክ ከተማ ለሽያጭ የሚቀርብ ሲሆን ከተቀመጠለት በላይ በሆነ ዋጋ ሊሸጥ እንደሚችል ይጠበቃል፡፡
አልበርት አንስታይን ኑክሌር ቦምቡ ከተሰራ በኋላ እንደተጸጸተ የተናገረ ሲሆን በተለይም በወቅቱ ኑክሌር ቦምቡ በአሜሪካ ብቻ መሰራቱን ሲያውቅ ጸጸቱ እንደባሰበት ገልጿል ተብሏል፡፡