የኑክሌር ጦርነት ቢቀሰቀስ ዓለም ምን ያጋጥማታል?
የኑክሌር ጦርነት አስከፊ እና መጠነሰፊ ችግሮችን ያስከትላል
አለምአቀፉ ማህበረሰብ እንዲህ አይነት አደጋዎች ለማስቀረት እንደ 'ነን ፕሮላይፈሬሽን ስምምነት' አይነት ስምምነቶችን ይጠቀማል
የኑክሌር ጦርነት ቢቀሰቀስ ዓለም ምን ያጋጥማታል?
የኑክሌር ጦርነት አስከፊ እና መጠነሰፊ ችግሮችን ያስከትላል።
እንደሰው' የኑክሌር ጦርነት የሚያስትለውን ችግር' በሰፊው ይዘረዝራል።
የመጀመሪያው ችግር፦ የኑክሌር ጦር መሳሪያዎች ሲፈነዱ መጠነሰፊ የሆነ ውድመት እና በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች እንዲሞቱ ሊያደርግ ይችላል። የኑክሌር ጦር መሳሪያው ፍንዳታ የሚያስከትለው ችግር በመሳሪያው መጠን ይወሰናል።
ጨረር(ራዲየሽን)፦ ፍንዳታው ለተፈጠረበት ቦታ ቅርብ የሆኑ እና ወዲያውኑ ያልሞቱ ሰዎች ለራዲየሽን ይጋለጣሉ፣ ለካንሰር ተጋላጭነታቸውን ይጨምራል።
ከዚህ በተጨማሪም የዘረመል ውድመትን ያስከትላል።
የአካባቢ ውድመት፦ የኑክሌር ፍንዳታ በአካባቢ ላይ ውድመትን ያስከትላል። የኑክሌር ፍንዳታ ከተከሰተበት ቦታ በ10 በሚቆጠሩ ኪሎሜትሮች ላይ ያሉ ሁሉንም ነገርች የሚያቃጥል ሲሆን ይህ የሬዲዮአክቲቭ ግጭትን በመፍጠር አየር፣ ውሃ እና አፈርን ይበክላል።
ኑክሌር ዊንተር፦ የኑክሌር ጦር መሳሪያ ስብርባሪዎች ጸሀይን በማጋረድ የዓለም የሙቀት መጠን ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ እንዲወርድ በማድረግ "ኑክሌር ዊንተር" የተባለው ክስተት እንዲፈጠር ሊያደርግ ይችላል።
ይህ ደግሞ ሰብሎች እንዲጎዱ በማድረግ አለምአቀፍ ድርቅን ሊያስከትል ይችላል።
ፖለቲካዋና አለምአቀፍ ደህንነት፦ በኑክሌር ጦርነት ማግስት የአለም ስርአት ሊናጋ ይችላል። ይህ በሚሆን ጊዜ ግጭት አና ትርምስ ስለሚፈጠር መንግስታት ቀውስ ውስጥ ሊወድቁ ይችላሉ።
በሰው ልጅ ላይ የሚኖረው አደጋ፦ በሰው ልጅ ላይ ከሚያስከትለው የሞት፣ የጉዳት፣ የስነልቦና ጫና እና ስደት ባሻገር የሚኖረው የረጅም ጊዜ የጤና ችግር ከባድ ነው።
መዳን እና ማገገም፦ የመዳን እድል በጦርነቱ መጠን እና ግለሰቦች ከፍንዳታው ቦታ ባላቸው ርቀት ይወሰናል። የማገገም ጉዳይ የረጅም ጊዜ ሂደት ሲሆን አስርት አመታትን አለያም ምዕተ አመታትን ሊፈጅ እንደሚችል ይገመታል።
ባዮዳይቨርሲቲ፦ በአካባቢ ስነ ምህዳር ብዙ ዝርያዎች እንዲጠፉ እስከማድረግ የሚደርስ ውድመትን ያስከትላል።
የኑክሌር ጦርነት የሚያስከትላቸውን ችግሮች ለመረዳት ብዙ ሳይንሳዊ ትንተናዎች እና እንደ ናጋሳኪ እና ሄሮሽማ ያሉ ታሪካዊ የድብደባ ሁነቶችን ማየት ይጠይቃል።
አለምአቀፉ ማህበረሰብ እንዲህ አይነት አደጋዎች ለማስቀረት እንደ 'ነን ፕሮላይፈሬሽን ስምምነት' አይነት ስምምነቶችን ይጠቀማል።