ፕሬዝዳንት ፑቲን የኑክሌር ጦር ልምምድ እንዲደረግ አዘዙ
ፕሬዝዳንቱ የጦር ልምምዱ እንዲደረግ ያዘዙት የምዕራባዊያን ሀገራት እንቅስቃሴ ስጋት ደቅኗል በሚል ነው
በዓለም ላይ ካለው 12 ሺህ የኑክሌር ጦር መሳሪያ ውስጥ 10 ሺህ ያህሉ በሩሲያ እጅ ላይ ይገኛል
ፕሬዝዳንት ፑቲን የኑክሌር ጦር ልምምድ እንዲደረግ አዘዙ።
የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የሀገራቸው ጦር የታክቲካል ኑክሌር ጦር ልምምድ እንዲደረግ አዘዋል።
የሀገሪቱ መከላከያ ሚንስቴር የጦር ልምምዱን አስመልክቶ ባቀጣው መግለጫ የምዕራባዊያን ሀገራት ተጽዕኖ እየጨመረ በመምጣቱ እንደሆነ አስታውቋል።
በልምምዱም የታክቲካል ኑክሌር ጦር ሙከራ እንደሚደረግም ተገልጿል።
የሚሳኤል አቀማመጥንም ጨምሮ በሚካሄደው በዚህ ልምምድ የባህር ሀይል ይሳተፋል የተባለ ሲሆን የጦር ልምምዱ በደቡባዊ ወታደራዊ ቀጠና በኩል ይደረጋል ተብሏል።
የሩሲያ የጦር ልምምድ በመግለጫው ልምምዱ የሀገሪቱን ግዛት አንድነትን እና ሉዓላዊነት ለማስጠበቅ እንደሚካሄድ አስታውቋል።
የሩሲያ- ዩክሬን ጦርነት በየጊዜው መልኩን እየቀያየረ የመጣ ሲሆን ፈረንሳይ ጦሯን ወደ ዩክሬን መላኳን አስታውቃለች።
የሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ጦር ወይም ኔቶ ወታደሮችን ወደ ዩክሬን መላክ የኑክሌር ጦርነት እንዲነሳ ምክንያት ሊሆን ይችላል ሲል የፈረንሳይን ውሳኔ ተቃውሟል።
ፕሬዚዳንት ፑቲን ከዚህ በፊት በሰጡት መግለጫ ሩሲያ በዩክሬን ምድር ከበርካታ ሀገራት ጋር እየተዋጋች መሆኗን እና ብሔራዊ ደህንነቷ አደጋ ውስጥ ከገባ የኑክሌር ጦር መሳሪያዎቿን እንደምትጠቀም አስጠንቅቀው ነበር።
ፕሬዝዳንቱ አክለውም የአሜሪካ እና ኔቶ ህብረት ዓለማችን ለሶስተኛው የዓለም ጦርነት አንድ እርምጃ ብቻ እንዲቀራቸው አድርጓልም ብለዋል።
ሩሲያ በኑክሌር አረር ትጥቅ ብዛት ከዓለማችን ቁጥር አንድ ሀገር በዓለም ላይ ካለው 12 ሺህ 100 አጠቃላይ የኑክሌር ጦር ውስጥ 10 ሺህ 600 ያህሉ በሩሲያ እጅ ላይ ይገኛል።