6ኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ ድምጽ የመስጠት ሂደት ተጠናቆ ቆጠራ እየተካሄደ ነው- ምርጫ ቦርድ
ከማለዳው 12 ሰዓት የተጀመረው ድምጽ የመስጠት ሂደት ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ ነው የተጠናቀቀው
ውጤት በምርጫ ጣቢያ ደረጃ እስከ ንጋት መገለጽ ይጀምራል
6ኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ ድምጽ የመስጠት ሂደት መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።
ከማለዳው 12 ሰዓት የተጀመረው 6ኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ ድምጽ የመስጠት ሂደት ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ መጠናቀቁን ቦርዱ አስታውቋል።
የድምጽ አሰጣጥ ሂደቱ ክምሽቱ 12 ሰዓታት ላይ መጠናቀቅ የነበረበት ሲሆን፤ የድምፅ አሰጣጥ ሂደት ዘግይቶ የተጀመረባቸው ቦታዎች በመኖራቸው፣ የድምፅ አሰጣጥ ሂደት ላይ የቁሳቁስ ስርጭት የዘገየባቸው ቦታዎች በመኖራቸው እና ድምፅ ለመስጠት ረጅም ሰልፉች ላይ ያሉ ዜጎች በመኖራቸው ነው የድምፅ አሰጣጥ ሂደት እስከ ምሽቱ 3 ሰአት ድረስ የተራዘመው።
በአሁኑ ሰዓትም በሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች የድምጽ አሰጣጥ ሂደቱ ተጠናቆ ቆጠራ መጀመሩንም ነው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ አሰታውቀዋል።
የምርጫ ውጤትም በጣቢያ ደረጃ እስከ ንጋት መገለጽ ይጀምራል ያሉ ሲሆን፤ “እንደ ጨረሱ ግን ሌሊት ወደ ምርጫ ክልሎች ይዘው እእንዳይሄዱና አድርገናል” ብለዋል።
“ቀሪ ውጤት ከስር ከስር እናሳውቃለን” ያሉ ሲሆን፤ “በ10 ቀን ውስጥ ቢያንስ ጊዜያዊ እናሳውቃለን” ሲሉም እታውቀዋል።
ኢትዮጵያ 6ኛው ዙር የተወካዮች ምክር ቤትና የክልል ምክርቤት ተወካዮች ምርጫ በዛሬ እለት ተካሂዷል።
በዛሬው እለት ከማለዳው 12 ሰዓት የተጀመረው የድምጽ አሰጣጥ ሂደቱ፤ በ673 የምርጫ ጣቢያዎች እስከ ምሽቱ 3 ሰዓት ተካሂዷል።
ምርጫ በሶማሌ ክልል ከምርጫ ቁሳቁስ ህትመት ጋር በተያያዘ እንዲሁም በትግራይ ክልል በተፈጠረው ግጭት ምክንያት ምርጫ 2013 አይካሄድም።
የሶማሌ ክልልና በተለያየ ምክንያት ምርጫ የማይሰጥባቸው ምርጫ ጣቢዎች ምርጫው ጳግሜ 1 ቀን 2013 ዓ.ም እንደሚካሄድ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ማስታወቁ ይታወሳል።
በምርጫ ከ38 ሚሊዮን ህዝብድምጽ ለመስጠት ተመዝግቧል፤45 የሚሆኑ የምርጫ ታዛቢዎች ምርጫውን ለመታዘብ እንዲሰማሩ ቦርዱ ገልጾ ነበር።