የፕሪሚየር ሊጉ ክለቦች በክረምቱ ዝውውር 2 ነጥብ 36 ቢሊየን ፓውንድ አውጥተዋል ተባለ
ይህም ከባለፈው አመት ቀጥሎ ለተጫዋቾች ዝውውር ከፍተኛ ወጪ የተደረገበት የዝውውር መስኮት አድርጎታል
በዝውውር መስኮቱ መዝጊያ ላይ 255 ሚሊየን ፓውንድ ወጪ መደረጉም ነው የተገለፀው
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች በክረምቱ የዝውውር መስኮት 2 ነጥብ 36 ቢሊየን ፓውንድ ለተጫዋቾች ግዥ ወጪ ማድረጋቸው ተነገረ።
ይህም ከባለፈው አመት የ440 ሚሊየን ፓውንድ ጭማሪ በማሳየት ሪከርድ ሆኖ ተመዝቧል ብሏል ዳሎይት የተሰኘው የፋይናንስ ተቋም።
የዝውውር መስኮቱ በተጠናቀቀበት በትናንትናው እለት ብቻ 255 ሚሊየን ፓውንድ ለተጫዋቾች ዝውውር ተደርጓል ነው የተባለው።
የፕሪሚየር ሊጉ 20 ክለቦች የዝውውር ወጪ አምስቱ የአውሮፓ ሊጎች (ላሊጋ፣ ቡንደስሊጋ፣ ሴሪኣ) ክለቦች ያወጡትን 48 ከመቶ ይሸፍናል።
ከፕሪሚየር ሊጉ እና ከፈረንሳይ ሊግ 1 ውጭ ሁሉም ሊጎች ከዝውውር ገቢያቸው ይልቅ ወጪያቸው ይበልጣል።
13 የፕሪሚየር ሊጉ ክለቦች ከ50 ሚሊየን ፓውንድ በላይ ወጪ የተደረገባቸውን ተጫዋቾችን አዛውረዋል።
ከ20ዎቹ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች 14ቱ ከባለፈው አመት የክረምት ዝውውር የበለጠ ወጪ አድርገዋል።
ይህም የፕሪሚየር ሊጉ ክለቦች ከኮሮና ወረርሽኝ በኋላ ገቢያቸው እያደገ መሄዱን ያመላክታል ብሏል ዴሎይት።
የእንግሊዝ ኮለቦች ለተጫዋቾች ዝውውር ከሚከፈል ክፍያ 550 ሚሊየን ፓውንድ አግኝተዋል፤ ይህም ከ2022 ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ከእጥፍ በላይ ጭማሪ ያሳየ ነው።
ከስፔን ላሊጋ ውጭ በግዙፍ የአውሮፓ ሊጎች ላይ የተመዘገበው የዝውውር ወጪ እድገት ያሳየ ነው ተብሏል።