የቱርኩ ፕሬዝዳንት በርዕደ መሬቱ ወቅት ለነበረው የነፍስ አድን ስራ መዘግየት ይቅርታ ጠየቁ
ፕሬዝዳንት ኤርዶጋን ርዕደ መሬቱን " የክፍለ ዘመኑ አስከፊ አደጋ " ሲሉ መግለጻቸው ይታወሳል
በርዕደ መሬቱ ርዕደ መሬት በቱርክ ብቻ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 44 ሺህ በላይ ደርሷል
የቱርክ ፕሬዝዳንት ኤርዶጋን በርዕደ መሬቱ የተጎዱትን ሰዎችን ነፍስ የማዳን ስራዎች ላይ ለነበረው መዘግየት ይቅርታ ጠየቁ፡፡
ፕሬዝዳንቱ ይህን ያሉት ይህን ያሉት በያዝነው ወር መጀመሪያ ላይ ባጋጠመው ርዕደ መሬት ኩፉኛ የተመታውን የሀገሪቱ ደቡብ ምስራቅ አድያማ አከባቢ በጎበኙበት ወቅት ሲሆን ከርዕደ መሬቱ በሕይወት የተረፉ የአከባቢው ሰዎች በእሳቸው ላይ የሰነዘሩትን ከፍተኛ ትችት ተከትሎ ነው፡፡
- የቱርክ እና ሶሪያን ርዕደ መሬት የተነበየው ሆላንዳዊ ቀጣይ ተረኞቹ እነማን ናቸው አለ?
- የቱርኳ አንታክያ ከሦስተኛው ርዕደ መሬት በኋላ ወደ ምድረ በዳነት ተቀየረች
የአዳሚያን ነዋሪው መህመት ዬልድሪም "ርዕደ መሬቱ ካጋጠመበት ጊዜ እስከ ሁለተኛው ቀን እኩለ ሌሊት ድረስ ምንም አይነት ነፍስ የማዳን ተግባራት አላየሁም" ሲል ቅሬታው መግለጹ ፍራንስ-24 ዘግቧል፡፡
"ማንም የመንግስት አካል አላየሁም፤ በጣም አዝናለሁ !" ሲልም ነበር የተናገረው ዬልድሪም፡፡
የነዋሪዎቹን ቅሬታ ያደረመጡት ፕሬዝዳንት ኤርዶጋን "በርዕደ መሬቱ እና በመጥፎ የአየር ጠባይ ምክንያት በአድያማ ውስጥ በመጀመሪያዎቹ ጥቂት ቀናት በአድያማ ውስጥ የምንፈልገውን መንገድ መስራት አልቻልንም:: ይቅርታ እጠይቃለሁ”ብለዋል፡፡
ያም ሆኖ የቱርክ መንግስት ለአደጋው የሰጠው የዘገየ ምላሽ ለምርጫ እየተዘጋጁ በሚገኙት አርዶጋን ላይ የሚፈጥረው ተጽእኖ ከባድ እንደሚሆን ይገለጻል፡፡
እንደፈረንጆቹ የካቲት 6 ባጋጠመው ርዕደ መሬት በቱርክ ብቻ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 44 ሺህ መድረሱ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡
በሬክተር ስኬል 7.8 የተመዘገበው አደጋ እንደፈረንጆቹ 1999 በሰሜን ምዕራብ ቱርክ ካጋጠመውና የ17 ሺህ ሰዎችን ህይወት ከቀጠፈው አደጋ የከፋ መሆኑ ይነገራል፡፡
እንደ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን አገላለጽ ከሆነ ርዕደ መሬቱ " የክፍለ ዘመኑ አስከፊ አደጋ "ነው፡፡
የተመድ ዋና ጸሃፊው አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በበኩላቸው የአደጋው መጠን እጅግ ከባድ መሆኑ ገልጸው ዓለም ለእርዳታ እጁን እንዲዘረጋ ጠይቀዋል፡፡
"አሁን አንድነት የሚያስፈልግብት ወቅት ላይ ነው ያለነው፤ ፖለቲካ የሚሰራበት ጊዜ አይደለም ፤ ሰፊ ድጋፍ እንደሚያስፈልግን ግልጽ ነው" ሲሉም ተናግረዋል ዋና ጸሃፊው፡፡