ቱርክ ፊንላንድና ስዊድን ቃላቸውን ስላልጠበቁ የኔቶ አባልነት ጥያቄያቸውን እንደማትቀበል ገለጸች
የተርክዬ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን ትናንት አርብ የኔቶ ዋና ፀሃፊ ጄንስ ስቶትንበርግን በኢስታንቡል ተቀብለዋል።
አውሮፓንና እስያን የምታማክለው የተርክዬ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን እና የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) አለቃ ጄንስ ስቶትንበርግ በኢስታንቡል መምከራቸው ተነግሯል።
- ቱርክ ፊንላንድና ስዊድን ቃላቸውን ስላልጠበቁ የኔቶ አባልነት ጥያቄያቸውን እንደማትቀበል ገለጸች
- ቱርክ ፊንላንድ እና ስዊድን ኔቶን እንዳይቀላቀሉ እንቅፋት ሆናለች ተባለ
ሐሙስ እለት ኢስታንቡል የገቡት የኔቶ ዋና ፀሃፊ የጥቁር ባህር እህል ስምምነት ማራዘሚያ እንዲሁም በስዊድን እና በፊንላንድ የኔቶ አባልነት ጥያቄ ላይ ያማከለ ጉብኝት ለማድረግ ቱርክዬ ገብተዋል።
ከሁለቱ መሪዎች ምክክር በኋላ ስቶትንበርግ ቱርክ “የጥቁር ባህር እህል ስምምነት”ን እንደገና ለማስጀመር የነበራትን ሚና አድንቀዋል።
በ ተርኪዬና የመንግስታቱ ድርጅት አደራዳሪነት ሩሲያ ዩክሬን የባህር ትራንፖርትን ተጠቅማ እህል ወደ ውጭ እንድትልክ እግድ ከታጠለች በኋላ ዳግም እንዲመለስ ማድረጓ ይታወሳል።
የኔቶ ዋና ፀሀፊ በትዊተር ገፃቸው "የፊንላንድና ስዊድን አባልነትን በሚጠናቀቅበት ሁኔታ ላይም ከፕሬዝዳንቱ ጋር ተወያይተናል ብለዋል።
ስቶትንበርግ ሐሙስ ዕለት ከተርኪዬ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሜቭሉት ካቩሶግሉ ጋር በኢስታንቡል ተገናኝተው መወያየታቸውንም አንዶሉ ዘግቧል።