በጋዛ ተኩስ አቁም የሚደረግ ከሆነ ቱርክ መልሶ የመገንባት ፍላጎት እንዳላት ኤርዶጋን ተናገሩ
ኢርዶጋን በተጨማሪም የአለም አቀፉ የኑክሌር ጦር መሳሪያ ባለሙያዎች ወደ እስራኤል እንዲሄዱ ጥሪ አቅርበዋል
"ተኩሱ የሚቆም ከሆነ በእሰራኤል የደረሰውን ውድመት ለማካካስ አስፈላጊውን ሁሉ እናደርጋለን" ሲሉ ኢርዶጋን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተናግረዋል።
በጋዛ ተኩስ አቁም የሚደረግ ከሆነ ቱርክ መልሶ የመገንባት ፍላጎት እንዳላት ኤርዶጋን ተናገሩ።
በጋዛ የተኩስ አቁም ስምምነት የሚደረግ ከሆነ ቱርክ የወደሙ መሰረተልማቶችን፣ ሆስፒታሎችን እና ትምህርት ቤቶችን መልሶ ለመገንባት ጥረት እንደምታደርግ ፕሬዝደንት ኢርዶጋን ተናገሩ።
"ተኩሱ የሚቆም ከሆነ በእሰራኤል የደረሰውን ውድመት ለማካካስ አስፈላጊውን ሁሉ እናደርጋለን" ሲሉ ኢርዶጋን ከጀርመን ጉብኝት መልስ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተናግረዋል።
በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ ኢርዶጋን እስራኤል የኑክሌር ጦር መሳሪያ መታጠቋን ወይም አለመታጠቋን ግልጽ እንዲያደርጉ ለጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ ጥሪ አቅርበዋል።
ኢርዶጋን በተጨማሪም የአለም አቀፉ የኑክሌር ጦር መሳሪያ ባለሙያዎች ወደ እስራኤል እንዲሄዱ ጥሪ አቅርበዋል።
ኢርዶጋን "እንደቱርክ ይህን ጥሪ እናቀርባለን። ከመዘግየቱ በፊት ጉዳዩ መጣራት አለበት። ይህን ጉዳይ እንከታተለዋለን" ብለዋል።
በሀማስ የታገቱት እንዲለቀቁላቸው እስራኤላውያን ቤተሰቦች ደብዳቤ እንደጻፉላቸው የገለጹት ኤርዶጋን የቱርክ ደህንነት ጉዳዩን እያየው ነው ብለዋል።
በዛሬ እለት ሀማስ፣ እስራኤል እና አሜሪካ ከአምስት ሳምንት በላይ ያስቆጠረውን ግጭት ለአምስት ቀናት ጋብ ለማድረግ መስማማታቸው ተገልጿል።
በእስራኤል እና ሀማስ ጦርነት እስካሁን ከ11ሺ በላይ ፍልስጤማውያን ተገድተናገሩ።