የቱርኩ ኢርዶጋን ጠንካራ ፉክክር ቢገጥማቸውም የሚበገሩ አልሆኑም
ለሁለት አስርት አመታት ቱርክን መምራት የቻሉት የቱርኩ ፕሬዝደንት ኤርዶጋን ያጋጠሟቸውን የፖለቲካ ፉክክሮች ሁሉ ማሸነፍ ችለዋል
ኤርዶጋን በፈረንጆቹ ግንቦት 14 በሚካሄደው የምርጫ ውድድር ጠንካራ ፉክክር ገጥሟቸዋል
ለሁለት አስርት አመታት ቱርክን መምራት የቻሉት የቱርኩ ፕሬዝደንት ኤርዶጋን ያጋጠሟቸውን የፖለቲካ ፉክክሮች ሁሉ ማሸነፍ ችለዋል።
በአሁኑ ወቅት በምረጡኝ ቅስቀሳ ላይ የሚገኙት ኤርዶጋን ያለፈውን ስማቸውን እና ስራቸውን በሀገሪቱ እየጠነከረ ከመጣው ተቃውሞ እየተከላከሉ ነው።
ኤርዶጋን በፈረንጆቹ ግንቦት 14 በሚካሄደው የምርጫ ውድድር ጠንካራ ፉክክር እንደገጠማቸው ሮይተርስ ዘግቧል።
ኤርዶጋን በሀገሪቱ ባለው የኢኮኖሚ ቀውስ እና በየካቲት ወር የተፈጠረው ግዙፍ የርዕደ መሬት አደጋ ተገቢ የግንባታ መመሪያ ተግባራዊ ባለመደረጉ የመጣ ነው በሚል ምክንያት ጠንካራ ትችት ቀርቦባቸዋል።
በቅድመ ምርጫ በተደረገ የናሙና ጥናት ምርጫው የኤርዶጋን ኤኬ ፖርቲ በፈረንጆቹ 2002 ምርጫ እንዳሸነፈበት ጊዜ ጠንካራ ፉክክር እንደሚኖር ያሳያል።
የኤርዶጋን ተቀናቃኞች፣ ኤርዶጋን አልሰራቸውም ያሏቸውን እየጠቀሱ የምረጡኝ ቅስቀሳቸውን አጧጡፈዉታል።
በቱርክ የተከሰተው ከፍተኛ የርዕደ መሬት አደጋ ከ50ሺ የሚበልጡ ዜጎችን ህይወት ነጥቋል።
ፕሬዝደንት ኤርዶጋን ተቃዋሚዎች ይህ ክስተት ለፖለቲካ አላማ ተጠቅመውበታል ሲሉ ይከሳሉ።
ፕሬዝደንት ኤርዶጋን የምርጫ ቅስቀሳቸውን በሀገሪቱ የለሙ ኢንዱስትሪዎችን እና መሰረተ ልማቶችን በመመረቅ አጅበውታል።